ከወክንድ የተሰጠ መግለጫ: ፀረ- ወያኔው ትግል ይፋፋም!

እኛ ወያኔ ከነግሳንግሱ ወደ ታሪክ ትቢያ እንዲወርድ ከመታገል ሌላ አማራጭ የለም ብለን በፅኑ የምናምንና በቀቢፀ ተሰፋ የተሞላን ሰላልሆን፣ ከወያኔ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን አንጠብቅም።  ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንዲሉ ወያኔና ሐቅ ሁሌም ለየቅል መሆናቸውን ጠንቅቀን እናውቃልንና። ዴሞከሪሲ ስንል የህዝብ ልዕልና፣ ነጻ ዳኝነት፣ የህግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ መበቶች መረጋገጥና የዜጎች እኩልነት እውን መሆን ማለት ነው።  የወያኔ ዴሞክራሲ ጭንጋፍ ሳይሆን ጨርሶ የማይፀነስ ለመሆኑ የህክምና መዝገበ-ቃላትን መግለጥ ከቶም አያይሻም።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …