ከዝንጀሮ ቆንጆ ቢመረጥ፥ ወያኔ አስቀያሚ ነው

ቢንያም ግዛው:  ሽቅብ ቁልቁል፣ተራራ እና ሸለቆ፣ሽርክት እና ለስላሳ ከፍ የማለት እና የማዘቅዝቅ፣ በሆነው ረዥም የአመታት ጉዞ በሀዘን ግዜ፣ በደስታ ግዜ፣ በመዝራት እና በማጨድ ወቅት፣ እንዲሁም በድህነት ወይም በሀብት ዘመን፣ ኑሮ የሌሊት ሲሆን የመከራ አሊያም የቀን ሲሆን የድሎት … በሁሉም አይነት አቅጣጫ የህይወት ዘመናቸው ሲያልፍ ሀገሬ ኑሪ! የሚለውን ቃል በልባቸው ላይ አትመው እትብታቸው ላረፈበት ምድር ቃል ኪዳናቸውን የጠበቁ ነበሩ። ከሀገራቸው ሰሜን እስከ ደቡብ ድንበሯን ለማስጠበቅ በእኩልነት ለሁሉም ዙሪያ ሲታገሉ፤ ሁሉንም በር ላለማስደፈር ማለዳ በምስራቅ ወጥተው ብርሀናቸውን ለምድሪቱ የፈነጠቁ። ለነገው ብርሀን ተሳምሊት በመሆን ማምሻውን በምዕራብ የዳመኑ የጨለሙ። ለምድራቸው፤ ከምድራቸው፤ በምድራቸው ሆነው በአድሎና በጎሰኝነት ሳንካ ሳያይሸበቡ ለሁሉም የኢትዮጵያ ክልል ዘብ የቆሙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች። ለሚተካቸው ትውልድ ደማቸውን በማፍሰስ በሉዐላዊነት አንድነቷን የጠበቀች ሀገር ያለ ባዕዳን ቅይጥ ባህልና ቋንቋ ሳትበረዝ ከአካልዋም ሳይቆረስ በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱትን የውስጥ እና የውጭ አንጃዎችን የመከቱ። በመስዋዕትነታቸው ህይወትን በሞት የዘሩ። የብዙ ቋንቋ፣ ባህል፣ ብሔር እና ሀይማኖት ምድር ብትሆንም ሁሉም እንዲቻቻሉ በማስተማር እና በመዘከር አንድ ክብርት ሀገር ገንብተው ያስተላለፏት የእኩልነት ቤት ኢትዮጵያ፤ዘመናትን ተሻግራ ከኖረች ወዲያ ዛሬ ላይ ባለቤት የሌላት ሆና ወይባለች። ያ ውበት እና ለዛዋ ተሟጦ ዜጋዋ የሚኖርባት ሳይሆን የሚማረርባት እና ተስፋ የማያይባት ምድር ሆና የአንድ ትውልድ እድሜን ያህል ማስቆጠርዋ አሁን ላይ በየስፍራው የተበተኑ አዛውንት ዜጎችዋ ምስክር ናቸው።  ሙሉውን  ያንብቡ