ከደብተራው ምንጮች: ወቅታዊ ዜና ቀመስ ቅኝት

ምንጮቻችን  እንደገለጹልን ወያኔ በመላው ኢትዮጵያ  የሚገኙ ብዙዎቹን የትግራይ  ተወላጆችን 1 ለ 5  በሚል  አደራጅቷል::  ይህም በአሻንጉሊቶቹ የተከበበት ኢህአዲግ ካለው መሰል  አደረጃጀት ጎን ለጎን ነው::  እነኝሁ  1 ለ 5  የተደራጁት  የወያኔ  አባላትም ወደዱም ጠሉም ቢያንስ  በሳምንት አንድ ጊዜ ለሚመደብላቸው  ሰው  ስለሚኖሩበት፣  ስለሚሰሩበት በአጠቃላይ ስላዩት፣ ስለሰሙት፣  ስለሰለሉት ዘገባ  (ሪፖርት) ያደርጋሉ::

ባለፈው እሁድ ከተካሄደውና  ወያኔ እራሱ ተወዳዳሪ፣  እራሱ ዳኛ  ሆኖ  ካሸነፈበት  የቀልድ ምርጫ ጋር በተያያዘም 20 ሺህ  የሚጠጉ  የትግራይ ተወላጆች የሆኑ  ሲቪሎች  መሳሪያ ታጥቀዋል  አዲስ አበባ ውስጥ::  እነኝሁ  አባላትም  የሚያወቋቸውን  ሰዎች ሁሉ “ካርድ ወስደሃል?  መርጠሃል ወይ?”  ወዘተ  የሚሉትን  ጥያቄዎች በመጠየቅና  በወግ  መልክ  በመሰለልና በመከታተል፣ ለተመደበላቸው  የወያኔ  አገናኛቸውም ዘገባ በማቅረብ ተጠምደው  ሰንብተዋል::  ሙሉውን ያንብቡ