ወቅታዊ ዜና ከፍኖተ ዴሞክራሲ ሬዲዮ

ጳጉሜ 2 ቀን 2008 ዓ. ም. (September 07, 2016)  – የወያኔ ባለስልጣኖች በመጪው ጥቅምት ወር ለይስሙላ ተቃዋሚ ድርጅቶች የተወሰኑትን ወንበሮች እንደሚያጋሩ ውስጥ አወቆች እየጠቀሱ ነው፡፡ በምን ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ ይህ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ባይሆንም ተግባራዊ ሊሆን ቢችል እንኳ የጉልቻ መለዋወጥ ከመሆን አያመልጥም ተብሏል፡፡ የህዝቡ ጥያቄ ወያኔ ሌባ ነው ስለዚህ ሌባ ደግሞ መወገርና መወገድ አለበት የሚል ነው፡፡ ሕዝቡ ከዚህ መለስ ድርድር እንደሌለ በተለያዩ አካባዎች ባካሄዳቸው ሕዝባዊ አመጾች መግለጹ የሚታወቅ ነው፡፡

ትናንት ጳጉሜ 1 ቀን የተጀመረውና ለአምስት ቀናት ይዘልቃል የተባለው የገበያ ማዕቀብና የቤት ውስጥ አድማ በተለያዩ ከተሞች ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ከየአቅጣጫው ከሚደርሱ ዜናዎች ለማወቅ ተችሏል። በየቦታው ሱቆች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን የትንራንስፖርት አገልግሎት መኪናዎችን ሌሎች አገልግሎት ስጭ ድርጅቶች ተዘግተዋል። በትናንትናው ዕለት ማዕቀቡን ባለማክበር በተንቀሳቀሱ መኪኖች ላይ መጠነኛ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ። በአንዳንድ ቦታዎች የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት እየዞሩ ዜጎችን ማስፈራራት የንግድ ተቋሞችን ለማስከፈት ጥረት ሲያደርጉ በአንዳንድ ቦታዎች የኃይል እርምጃ ከመውሰድ አንስቶ አፍሶ እስከማሰር ደርሰዋል። ከሁለት ቀን በፊት በወለጋ የስው ህይወት እንደጠፋ የተዘገበ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ሁለት ሰዎች በደምቢ ዶሎ በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች እንደተገደሉ መረጃ ድርሷል።

በቅሊንጦ እስር ቤት የሞቱት ሰዎች ማንነት እስካሁን በወያኔ አገዛዝ በኩል የአልተገለጸ ሲሆን ስለቤተሰቦቻቸው ሁኔታ ለማወቅ የሚጠይቁትን የእስራኞች ቤተሰቦች ማንገላታት እንደቀጠለ መሆኑ ይነገራል። በዛሬው ፤ዕለት ቤተሰቦቻቸው በህይወት መኖራቸውን ለማወቅ በእስር ቤቱ ተገኝተው የነበሩትን ዜጎች ፖሊሶች ከመደብደባቸውም በላይ ገሚሶችን አስረው የወሰዱ ሲሆን ሌላው እንዲበታተን አድርገዋል።

በባህር ዳር ወጣቶችን ከየቤቱ እያወጡ ማሰር የቀጠለ ሲሆን ዛሬ የተያዙ ወጣቶች ወደ ብር ሸለቆ ሊወሰዱ ሲዘጋጁ ቤተሰቦች የአባይ ድልድይን ዘግተው ወጣቶች እንዳወሰዱ አድርገዋል።

የአፍሪካ የሰብአዊ መብትና የሕዝቦች መብት ኮሚሽን የሚባለው ድርጅት የወያኔ አስከፊ አገዛዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ያደረሰውን የግፍ ድርጊቶች ዘርዝሮ በማጋለጥ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ኮሚሽኑ ለደረሰው በደል ነጻና ገለልተኛ የሆነ ኃይል እንዲመረምር፤ ትክክለኛ የፍርፍ ሂደት እንዲኖር፤ የሕዝብ ሀሳብን የመግለጽ የመሰብሰባና መረጃ የማግኘት መብት እንዲከበር፤ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ጉዳት የደረሰባችው ወገኖች ካሳ እንዲከፈላቸው፤ አገዛዙ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ግዴታዎችን እንዲያከበር ጠይቋል።

የአረመኔው ነጋዴ የአላሙዲ ንብረት የሆነው ኤልፎራ በተሰኘው የዶሮ እርባታ ውስጥ አደገኛ የዶሮ ወረርሽኝ በሽታ በመከሰቱ በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ሠራተኞቹ በአጠቃላይ ዶሮዎቹ ለአዲስ አመት ገበያ ላይ እንዳይወጡ ያደረጉት ጥረት ተቀባይነት አለማግኘቱ ታወቀ፡፡ የዶሮ ወረረሽኝ በሽታ ምንነቱ በትክክል ያልታወቀ ቢሆን ሳልሞኔላ የሚባለው ገዳይ በሽታ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለ። በአሁኑ ሰአት በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ ዶሮዎች በአጠቃላይ ተቃጥለው ሊወገዱ ሲገባ የድርጅቱ የገንዘብ ጥቅም ላይ በማተኮር ሕዝብ በሽታው እንዲለከፍ ለማድረግ በአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶች ላይ በመኪና ወጥተው እንዲሸጡ መወሰኑ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና ሕዝብን ለመጨረስ ሆን ተብሎ ከወያኔ ባለስልጣናት ጋር የተሸረበ ሴራ ሊሆን እንደሚችል የድርጅቱ ሠራተኞች ያስረዳሉ፡፡ ይህንን መረጃ በተቻለ ፍጥነትና አቅም ለሕዝብ ማዳረስ ወገንን ከሞትና ከበሽታ መታደግ እንደሆነ የዶሮ እርባ ባለሙያዎች ማስጠንቀቂያ አዘል ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡

የመጪው አመት የትምሕርት ዘመን ከመደበኛ የመከፈቻ እለቱ ሊዘገይ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ የሆነው የትምህርት ቤቶቹ መከፈት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተፋፋመ በመሄድ ላይ ላለው ህዝባዊ አመጽ አመች ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል ከሚል ስጋት መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ያስዳሉ፡፡ ወያኔ መምህራንና ተማሪዎችን ለአስራ አምስት ቀናት በስብሰባ ሊወጥር ቢዘጋጅም ስብሰባዎቹ ሌላ የሕዝባዊ አመጽ አማራጮች ሊሆኑ ስለሚችሉ ላይካሄዱ ይችላሉ የሚል ግምትም በስፋት እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ዝርዝ ዜና

ይህን ተጭነው ያዳምጡ