ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እየተደገሰልን ነው የሚል ጭምጭምታ አለ

(ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ) – አመጹ በመቀጣጠሉና ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ እየወጡ በመሄዳቸው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊካሄድና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅ እንደሚችል ከምዕራብ አገሮች የጸጥታና የዲፕሎማሲ ምንጮች ወሬዎች እየተናፈሱ መሆናቸው ይሰማል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ማንኛውም ዓይነት መገናኚያ የሚቋረጥ መሆኑና የሰዓት ዕላፊ አዋጅ እንደሚታወጅ እንዲሁም የጅምላ እስራት በተለይም በወጣቶች ላይ እንደሚካሄድ የተገኘው ዜና ይጠቅሳል። ሕዝባዊ አመጹ እየተቀጣጠለ መምጣቱ የወያኔን መሠረት ክፉኛ እየናደ መምጣቱ ግልጽ ሲሆን መፈንቅለ መንግሥት ያደርጋሉ የተባሉት ከማን ወገን መሆናቸው ግልጽ አይደልም። የወያኔን እድሜ ለማራዘም መውጫው መንገድ ብለው ካሰቧቸው እቅዶች መካከል አንዱ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት ብዙዎች ይሰጣሉ። ይህንንና ሌላም ዜና በዝርዝር ያንብቡ  ወይም ያዳምጡ.