ወያኔን ለማዳን አንጃ ሕዝቡን ማደናገር ጀመሯል

ቴድሮስ አባቡልቻ: “አፈዴቪት ፈርመን ከወያኔ ጋር እንተባበር” ባዮ አንጃ ዛሬ ደግሞ የሕዝቡን ቆራጥ ሁለ-ገብ ትግል ለማጨናገፍና ወያኔን ከውድቀት ለማዳን እኩይ ስራውን መጀመሩን በኢትዮሚዲያ ላይ “ለትግራይ ምሁራን የቀረበ ጥሪ” የሚል በቅርጹም ሆነ በይዘቱ አዘናጊ ዝባዝንኬ ጽሁፍ ለጥፏል። በመጀመሪያ ጥሪው በራሱ ደካማና ሚዛን የማይደፋ ነው። የትግራይ ምሁር ባይ ነን የሚሉት አይደሉም እንዴ ወያኔን እየመሩ ያሉት? የትግራይ ሕዝብ በትግራይ ምሁራን ጥሪ ይነቃል ማለት ደግሞ ሰፊውን የትግራይ ሕዝብን መናቅና መዝለፍ ነው። እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ ተወላጆችም በወያኔ ክፍተኛ ግፍ ተፈጽሞባቸዋል አሁንም እየተፈጸመባቸው ነው። የአዲስ አበባ ሕዝብ በከባድ የወያኔ አፈና ስር በመሆኑ እንደ ጎንደሩ፣ ኦሮሞው. . . ወዘተ ላመጽ ባለመነሳቱ “ለአዲስ አበባ ምሁራን የቀረበ ጥሪ” ሊቀርብለት አይገባም። ለትግራይ ሕዝብ መበደል፣ መራብ፡ በበሽታ መሰቃየት የትግራይ ምሁር ቆዳ አይሰማውም። ምሁሩ ቀረቤታው – ሁሉም ባይባል – ለገዢው መደብ ነው። ባጭሩ ጥሪው ኢላማውን የሳተ መሆኑ መታወቅ አለበት።  ሙሉውን  ጽሁፍ ያንብቡ …