ወያኔ ባዕዳን ወታደሮች ሊያስገባ አስቧል፣ ከ13 ሺ በላይ እስረኞች፣ የኤች አይ ቢ በአስደንጋጭ መጨመር፣ በትውልድ ኢትዮጵያዊያን መብት ተነፈጉ

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ (ኅዳር 4 ቀን 2009 ዓ.ም.) – ወያኔ የባዕዳን ወታደሮችን ሊያስገባ ማሰቡ ተጋለጠ – የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፖእአኮ) ከ13 ሺ ሰዎች በላይ መታሰራቸውን ገለጸ –  የኤች አይ ቪ በሽታ በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ – በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በባንክ፣ በኢንሹራንስና በተመሳሳይ የንግድ ተቋማት ባለድርሻነት መብት ተነፈጉ – ፖሊሶችና ወታደሮች በዘረፋ ተግባር ላይ መሰማራታቸውን ወያኔ በይፋ አመነ – የወያኔ ባለስልጣኖች በመምህራን ላይ እያካሄዱት ያለው የእስራት ዘመቻ አለም አቀፍ ውግዘትን ሊያስከትል ይችላል ተባለ – የኢንዱስትሪ መንደሮች አካባቢውን የሚበክሉና የነቀርሳ በሽታ ምንጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ – የኢንተርኔት አገልግሎትና ሶሻል ሚዲያ እስከወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል የሚል ስጋት አለ – በሱዳኑ አልበሽር ላይ ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ ወያኔም ይጎዳዋል።

ወያኔ የባዕዳን ወታደሮችን ሊያስገባ ማሰቡ ተጋለጠ ፋብሪካቸውን እንዲጠብቁ በሚል ሰበብ ወያኔ በብዙ መቶ የሚቆጥሩ የቱርክና የቻይና ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ፈቃድ ለመስጠት ፍላጎት ያለው መሆኑ ተጋለጠ። ይህን በተመለከተ ከቱርኮች ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለው የወያኔው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ከቱርኮች ጋር ንግገር መጀመሩ ሲነገር ከቻይና ጋር ደግሞ በአዲስ አበባ፤ ቤጂንግና ጅቡቲ ግንኙነት መጀመሩ ተዘግቧል። ወያኔ በሕዝብ ትግል ሲወጠር ባዕዳንን ጣልቃ ሊያስገባ መወሰኑ የሚያስገርም አይደለም ያሉ ክፍሎች ግን በባዕዳን ላይ ይዞታዎች ላይ የተጀመረው ጥቃት መቀጠልና መፋፋሙ አስፈላጊ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፖእአኮ) ከ13 ሺ ሰዎች በላይ መታሰራቸውን ገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፖእአኮ) በሰጠው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ወዲህ ወደ 13 ሺ ዜጎች ከየቦታው ታፍሰው ታሰራቸውን አጋልጦ አድማ ሲያዘጋጁ ተድረሶባቸዋል በሚል ምክንያትና የኢሕአፓ አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ወጣቶች መታገታቸውን ገልጿል። የድርጅቱ መሪ አቶ አሊ ሁሴን በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን እስርና እንግልት በተመለከተ ኦሮሚያ በሚለው አፋቸው ሌሎችን ማንሳት አቅቷቸው መገኘቱ በጣም አሳሳቢ ነው ካሉ በኋላ በጎንደር፤ ጎጃም፤ ሰሜን ሸዋን ወሎ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበብና በደቡብ ከተሞች በዙዎች ለስርና ግብረስየል መጋለጣቸውን አስረድተዋል።

የኤች.አይ.ቪ. ስርጭት በሚያስደነግጥ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን በበሽታው ላይ ጥናት ያካሄዱ ተመራማሪዎቹ አስታወቁ፡፡ ሰሞኑን ይፋ ከተደረጉ ጥናቶች መገንዘብ የተቻለው በትላልቅ ከተሞችና በመለስተኛ ከተሞች በተደረጉ ጥናቶች በሽታው ወጣቶችንና ታዳጊ ወጣቶችን በወረርሽኝ ዓይነት ሁኔታ እያጠቃ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በናዝሬት፣ በጂማ፣ በሀዋሳ፣ በዲላ፣ በአርባ ምንጭ ወዘተ. በበሽታው የሚጠቁ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን ለረጅም አመታት በበሽታው ላይ ጥናት ያካሄዱ ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡ ለበሽታው መስፋፋት ዋነኛ ሰበቦች መሆናቸው የተጠቀሱት የተለያዩ የአደንዛዥ እጾች በስፋት በወጣቶች አካባቢ እንዲስፋፉ መደረጋቸው አንዱና ዋነኛው ሲሆን ከዚሁ ጋር ልቅ የሆኑ የዳንኪራ ቤቶች እንደ አሸን መፍላታቸው መሆኑ በቀረቡት ጥናቶች ላይ ተወስቷል፡፡ ሌላው የወያኔ ባለስልጣናት ከአንድ የህንድ ኩባንያ ጋር በመመሳጠር ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቧቸው ቀዳዳ ኮንዶሞችም የራሳቸው ድርሻ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ወያኔ የወጣቱን ስነልቡና ለማሽመድመድ ወጣቱን ለተለያዩ ሱሶች ተገዢ እንዲሆን በስልት እየሰራ መሆኑን በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ያስረዳሉ፡፡

የውጪ አገር ዜጎች በባንክ፣ በኢንሹራንስና በሌሎች ተመሳሳይ የንግድ ተቋማት የባለድርሻነት መብት እንዳይኖራቸው ተደነገገ፡፡ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በግል ባንኮችና ኢንሹራንስ ድርጅቶች ውስጥ ባለድርሻዎች መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ አሁን የወያኔ አገዛዝ ባወጣው እገዳ ያላቸውን ድርሻ መውሰድ ወይም ከቦንኮቹ ጋር ተስማምቶ በጨረታ ድርሻቸውን መሸጥ ይገደዳሉ፡፡ ይህ ሁኔታ እየሰፋ እንደሚሄድና በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወያኔ የተዘጋጀውን ቢጫ ካርድ በየአመቱ በመግዛትም ሆነ ወያኔ በየኤምባሲዎቹ በሚያዘጋጀው ፀረ- ኢትዮጵያ ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ለወያኔ ድጋፋቸውን የማይገልጹ ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዳይሆኑ እግድ ይጥላል፡፡ ወያኔ ይህን ሁኔታ እንዲህ ባፈጠጠ መልኩ ለመግፋት የተገደደው በውጪ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ባለፉት አራት ወራት በአውሮፓና በአሜሪካ የሚያደርጉት የተቃውሞ ሰልፍ እየሰፋና እጠነከረ እንዲሁም ተሰሚነትን እያተረፈ በመሄዱ መሆኑን የፖለቲካ አዋቂዎች አስተያየታቸው ይቸራሉ፡፡ ፖሊሶችና ወታደሮች በዘረፋ ተግባር ላይ መሰማራታቸውን ወያኔ በይፋ አመነ፡፡

ወያኔ ፖሊሶቹና ወታደሮቹ በዘረፋ ተግባር ላይ መሰማራታውን በይፋ አመነ፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወያኔ ለውጪ ምንዛሪ ኪሳራ የዳረገውን ማንኛውም የውጪ ሀገር ዜጋ ሲንቀሳቀስ ወያኔን ማሳወቅ እንዳለበት የደነገገውን የህግ አንቀጽ መሰረዙን ባስታወቀበት ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮች የወጣውን አዋጅ አጋጣሚነት በመጠቀም ዜጎችን መዝረፋቸውን ወያኔ ቢያምንም ይህን ውንብድና በፈጸሙት ላይ ግን በተለመደው ሁኔታ ምንም እርምጃ አለመውሰዱ ታውቋል፡፡ የውጪ ሀገር ዜጎች እንደልባቸው እንዲጓዙ የፈቀደበት ሁኔታ የሀገሪቱ ፀጥታ አስተማማኝ በመሆኑ እንዳልሆነና የውጪ ምንዛሪ እየተሟጠጠ በመሄዱ እንደሆነ በርካቶች ይናገራሉ፡፡ የወያኔ ባለስልጣኖች በመምህራን ላይ እያካሄዱት ያለው የእስራት ዘመቻ አለም አቀፍ ውግዘትን ሊያስከትል ይችላል ተባለ፡፡

የወያኔ ባለስልጣኖች በዘመቻ መልክ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ መምህራንን ላይ የሚያካሂዱት እስራትና አፊና ዓለም አቀፍ ውግዘት ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ ትምህርት በአፍጢሙ እየተደፋ ባለበት መምህራንን በተናገሩት፣ የወያኔን ዘረኝነት፣ ዘራፊነትና ነፍሰ-ገዳይነት መረጃ አስደግፈውና ብጥርጥር አድርገው እራሱ ወያኔ በሰበሰባቸው ሰብሰባዎች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አለኝታነታቸውን በማስመስከራቸው በወያኔ እየተገደሉ፣ እታሰሩና ጥቂት የማይባሉ መምህራን እየታፈኑ በውል በማይተወቁ እስር ቤቶች በስየል ቁም ስቅላቸውን እያዩ መሆናቸውን ከሚደርሱን መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ የአረመኔው የወያኔ ወንጀል ዓለም ዓቀፍ ውግዘትና ማእቀብ ሊደረግበት እንደሚችል የትምህርት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ የኢንዱስትሪ መንደሮች አካባቢውን የሚበክሉና የነቀርሳ በሽታ ምንጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡

ወያኔ የኢንዱስትሪ መንደር እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው ውሎ አድሮ አገር በካይና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ለተለያዩ የነቀርሳ በሽታዎች የሚዳርግ እንደሆነና ሊወገዝ እንደሚገባው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች አስጠነቀቁ፡፡ በእነዚህ የኢንዱስትሪ መንደሮች በተባሉት የሚተከሉት ፋብሪካዎች በካርቦንዳይ ኦክሳ የአየር ንብረትን በመበከል በየአመቱ በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት መቀጠፍና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ በተለያዩ የነቀርሳ በሽታዎች እንዲማቅቁ የሚያደርጉና እንደ ቻይና የመሳሰሉ አገሮችን እድገት ጥያቄ ውስጥ ያስገቡ ዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ ያላቸውን ፋብሪካዎች ከቻይና ነቃቅለው በማምጣት ኢትዮጵያ ውስጥ በመትከል የአካባቢውን አየር ንብረት በመበከል የኢትዮጵያ ድሀ ገበሬዎችን በነቀርሳ በሽታዎች በቁራኛ እንዲያዙና እንዲማቅቁ የተደረገ ፀረ-ሕዝብ ሴራ መሆኑ ሊስተዋልና ሊወገዝ ይገባዋል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎትና ሶሻል ሚዲያ እስከወዲያኛው ሊዘጋ ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡

የኢንተርኔት አገልግሎቶችና ሶሻል ሚዲያዎች ግብአተ መሬት እንደገቡና እስከወዲያኛው ተዘግተው እንደሚቆዩ ከውስጥ አወቆች ጥቆማ መረዳት ተችሏል፡፡ ወያኔ የቻይናን የሶሻል ሚዲያ ማለትም የፌስቡክ፣ የኢንስታግራም፣ የቫይበር፣ የኋትስአፕና የመሳሰሉትን ልምድ ሥራ ላይ አውሎታል፡፡ በዚህ የኢንተርኔት አፈና በደምሳሳው ስሌት ወያኔ ያገኝ የነበረውን ከሰማንያ ሚሊዮን ብር በላይ ማጣቱ ታውቋል፡፡ ወያኔ በሳተይላት የሚሰራጩ የተቃዋሚ የቴሌቪዥን ስርጭቶችን ማየት ክልክል መሆኑንና በሳተላይት የሬድዮ ስርጭቶችን ማድመጥ ቢከለክልም ሕዝቡን ከማየትና ከማድመጥ ማስቆም አለመቻሉን በመረዳት በየቤቱ እየዞረ ከሳተላይት መቀበያ የሆነውን አል. ኤን.ቢ. የሚባለውን በተወሰኑ ሰፈሮች ከሳተላይት መቀበያ ሰሀኖች ላይ በፌደራል ፖሊሶች አማካኝነት እያስነቀለ መሰብሰቡ የሚታወስ ነው፡፡ ወያኔ ከዚህም አልፎ ፍኖተ ዴሞክራሲን፣ ኢሳትን የመሳሰሉትን ስርጭቶች በሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካ ዶልር በመክፈል ባለፉት ሰሞናት ለተወሰኑ ሰዓታት ለማፈን ጥረት ማደረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ድርጊት የቃሬዛ ላይ መንፈራገጥ ከመሆን የማይዘል መሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ በሱዳኑ አልበሽር ላይ ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ ወያኔም ይጎዳዋል ተባለ፡፡

የሱዳኑ የአልበሺር ቡድን ላይ ሕዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱ ወያኔንም እየናጠው መሆኑ ሊሳት እንደማይገባው ታወቀ፡፡ ሱዳን የነዳጅ ድጎማን በማንሳቷና የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ በመድረጓ ባሳለፍነው ሰኞና ማክሰኞ በአትባራ፣ በዋድ ማዳኒ፣ በኒያላና በካርቱም ሕዝባዊ ተቃውሞዎች መካሄዳቸውን ከስፍራው ከደረሱን ዘገባዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡ የሱዳኑ አምባገነን አል በሽር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በወያኔ ጋሻጃግሬነት በመድፈር የጎንደርን መሬት ቆርሶ የወሰደና በየጊዜው ወታደሮቹን የኢትዮጵያን ድንበር እያዘለቀ በርካታ ገበሬዎችንና ነጋዴዎች የጨፈጨፈ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደመኛ ጠላት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ አል በሺር በሱዳን ተሰደው ተጠልለው የነበሩ የኢሕአፓ አባላትንና እንደነ ሻለቃ አጣናው ዋሴን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት ያስገደለ አረመኔ መሆኑ የሚታሰው ነው፡፡ አሁን በሱዳን የተከሰተው ሕዝባዊ አመጽ እየጸናና እየተጠናከረ መሄዱ አይቀሬ መሆኑን በርካቶች ያስረዳሉ፡፡ የአልበሽር ቡድን መመታት ወያኔንም ያልፈሰፍሰዋልና ግም ለግም እንዲሉ፣ አረመኔ ለአረመኔ ተቃቅፈው መሰናበቻቸው መቅረቡን ያለው ሁኔታ አመላካች መሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡

በኦጋዴን ያለው ተለጣፊ ፓርቲ ወያኔ የሚያካሂደውን ጸረ ሕዝብ ዘመቻ ሙሉ በሙሉ በመደገፉ ሙሉ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን የፓርቲው መሪ አብዲ ኢሌይ ተቃዋሚዎቹ የሆኑትን አምስት የጽህፈት ቤት አባሎች ሊያባርር ማቀዱ ታውቋል። ከዚህ ቀደም ይህን እርምጃ የፌዴራል ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረው ካሳ ተክለብርሃን ከልክሎት የነበረ ሲሆን የብአዴኑ ካሳ ወደ ጎን ሲደረግ ግን አብዲ የፈለገውን የማድረግ መብት በወያኔ ተሰጥቶታል ያሉ ክፍሎች የሶማሌ ክልል አረመኔ ልዩ ሀይልም ወደ ሀረር ጦር መላኩን አጋልጠዋል ።

ልዩ ልዩ

ወያኔ ወደ ሶማሊያ ያስገባውን ጦር በክፍያ ማነስ አሳቦ እየመለሰ ቢናገርም ዋና ችግር ሕዝባዊ አመጹ የመጣበት ውጥረት ነው ያሉ ክፍሎች የወያኔ ጦር ሲወጣ አል ሸባብ ወዲያውን ቦታውን ከመያዙ በተጨማሪ ከወያኔ ጦር ተባብረዋል ያላቸውን በካርታ ነጋዴዎች ይዞ እንዳረዳቸውም ለማወቅ ችሏል። ወያኔ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሆነው አሚሶም ተብሎ ከሚጠራው ኃይል ስር 4ሺ 400 ወታደሮች ሲኖሩት በአሚሶም ያልተጠቃለሉ ወደ 6ሺ የሚጠጉ ሰላዮች፤ወታደሮችና ነጋዴዎችም በሶማሊያ እንዳሉት ይታወቃል። በተመሳሳይ ዜና ደግሞ ለጅቡቴ ገሌህ እለግሳለሁ ያላቸውን የኮማንዶ ወታደሮች እንደማይልክ ለኦማር ገሌህ አስውቋል ተብሏል። ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ ከነጻ ሀገር ነኝ ባይዋ ከሶማሊላንድም ጋር ንትርክና እሰጥ አገባ መግባቱ ተዘግቧል ። የወያኔ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሶማሊላንድን መሪ ሲላዮንና ሌሎች ሚኒስትሮችንም አዲስ አበባ ጠርቶ ሊደነፋባቸው መሞከሩም የወያኔ ፖለቲካ ዝብርቅርቅና ያልተጠና መሆኑን ያሳያል ሲሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል። በበርበራ ወደብ ግንባታ ከግብጽና ካታር ጎን በመሆን ድጋፉን የገለጠው ወያኔ የበርበራና የሀርጌሳ አውሮፕላን ማረፊያዎች ለኩዌት ሊሰጡ መታሰቡን በመቃወም ሶማሊላንድን ሊያስፈራራ ሞክሯል። ሥደተኞችን እያፈሰ ለወያኔ መስጠት ልማዱ የሆነው ሲላንዮም በተግባሩ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ ተሰጦታል።
በሱዳን የኦማር በሺር አገዛዝ በየመኑ ጦርነት የሳውዲን ጦር ለመደገፍ ከአንድ ሺ በላይ ወታደር በማሰለፉ ሳውዲ የበሽር መንግስት በዳርፉርና በሱዳን ሕዝብ ነጻነት ድርጅት (ኤስፒኤልኤ–ሰሜንን) ላይ ለሚያካሂደው ጦርነት የተወሰነ ቢሊዮን ዶላር ልትረዳ ተስማምታለች ተባለ ። በሺር ችግሮቹ በሰላም አይፈታም ብሎ ማመኑን በቅርቡ ሳውዲ ንጉስን ያገኘ ጊዜም ገልጾለታል ተብሏል ። ሻዕቢያም የመንና ኢራንን ከድቶ ከሳውዲ ጋር በመሰለፉና አሰብንም አሳልፎ በመስጠቱ ከሳውዲና ካታር ብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እያገኘ ነው ያሉ ክፍሎች ሳውዲ አረቢያ በአፍሪካ ቀንድ ጣልቃ ገብነቷ እያየለ ነው ብለዋል ። በሺርም ወያኔም አዲስ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የሚሆነው ዶናልድ ትራምፕ በጸር ሽብርተኛ ሰበብ ከጎናችን ይቆማል ብለው ተደስተዋል ብለዋል ያሉ ታዛቢዎች የአሜሪካ ፖለቲካ በአካባቢው ቀውስ ውስጥ ሊገባ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ። ትራምፕን ደግፎ በር ጽፎ የነበረው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርም ከሰሜን ኮሪያ መሳሪያ ሊቀበልና ወታደራዊ እርድታ ሊያገኝ ተዘጋጅቷል ያሉ ውስጠ አዋቂዎች የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በአስከፊ ሁኔታ ተፋፍሟል ሲሉም ገልጸዋል።

ዝርዝር ዜና ያዳምጡ