ወያኔ አሸባሪነቱን እባብ ተናዳፊነቱን አይተውም!

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅተ (ኢሕአፓ ወክንድ) መግለጫ – የወያኔ ፍጹም እምነትና ተልዕኮ ምን እንደሆነ ለማያውቁ እንዲያውቁ ለሚያውቁም እንዲያገናዝቡ ቀደም ብሎ ተደጋግሞ ቢነገርም ይህ ዘረኛ ቡድን የተካነበትን የማጭበርበሪያ ስልት በቅጡ የተረዳው ቁጥር ሰፊ እንዳልነበረ ይታወቃል። ለ27 ዓመት ሰላምን ከምድሪቱ ያጠፋ፣ ኢትዮጵያን የጨለማ ማቅ ያለበሳት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አስሮ ለጆሮ በሚዘገንን ግብረ-ስየል አሰቃይቶ ከሰውነት ውጭ እንዳላደረገ፣ በሺዎቹ የሚቆጠሩትን ዜጎችን ህይዎት ልዩ ነብሰ ገዳይ ቡድን አሠማርቶ (በስደት ዓለም የነበሩም ጭምር) እንዳላጠፋ፣ ዜጎች መብታችን ይከበር፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣አትከፋፍሉን፣ የትግሬ የበላይነት ይቁም፣ በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግቡ፣ ድምጻችን ይሰማ በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ስለወጡ የአሸባሪነት ታፔላ እየለጠፈ ወደ ማጎሪያዎቹ እንዳላጋዘ፣ የሕዝብን የዜግነት መብት ረግጦ ስንቱን አማራ ለፍቶ ከሠራው ቦታ አፈናቅሎ እንደናዚዎቹ በገፍ እንዳላጋዘና እንዳልጨፈጨፈ፣ አሁንም ይህንን ፋሽስታዊ ድርጊቱን በወታደራዊ እዝ አጠናክሮ ዜጎችን እየፈጀ ያለና አገርን ሠላም ያሳጣ አረመኔ አገዛዝ፣ ከሰሞኑ እያስደመጠ ያለው የሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ ዲስኩር ከዚሁ አገዛዝ ሲሰማ ጆሮ የሚያደማ ብቻ ሳይሆን ለህዝብ ያለው ንቀት የደረሰበትን ደረጃአጉልቶ የሚያሳይ ነው።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ . . .