በጎንደር ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

የወያኔን አፈና፣ እመቃ፣ ማሰፈራራት በወኔ  እምቢ በማለት ዛሬ  በታሪካዊቷ  የጎንደር ከተማ  ታላቅ ህዝባዊ የተቃውሞ  ሰልፍ ተካሂዷል።   ህዝቡ ወያኔና  አሳዳሪ  ጌቶቹ ጸረ-ኢትዮጵያ ባዕዳን  የሚጠቀሙባቸውን ቋንቋ፣ ሀይማኖት እና  ሌሎችም የመከፋፈያ  ስልቶች በጣጥሶ  በመጣል አንድነቱን ለወዳጅም ለጠላትም አሳይቷል።  በአገዛዙ የታሰሩት የወልቃይት ጠገዴ  ማንነት አሰተባባሪ  ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ ህዝቡ ያነሳው የማንነት ጥያቄ እንዲከበር፣ ከሀገሩ እየተሰረቀ  ለባዕዳን የተሸጠው መሬትና  ንብረት እንዲመለስ ጠይቋል።  በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል በኦሮሞ ወንድም እህቶቹ ላይ የሚደርሰውን ግድያ  አውግዟል።  የሻዕቢያ ተላላኪ ወያኔ  እንጅ የወልቃይት ጠገዴ  ህዝብ እንዳልሆነ  ገልጹዋል።  በአጠቃላይ በሰልፉ ላይ የተገኙ አንድ ወገናችን  ሁኔታውን ሲገልፁልን፣ እምባ  እየተናነቃቸው እንዳሉት ”በዘመነ መሳፍን ወቅት ማዕከላዊ  መንግሥቷ  ተዳክሞ፣  በየአካባቢው  ሹማምንት የርስ በርስ ሽኩቻ  ሰበብ በጦርነት ትታመስ የነበረችውን ኢትዮጵያ  ዳግም አንድ አድርገው የዘመናዊት ኢትዮጵያን ብርሃን የለኮሱትን አባ ታጠቅ ካሳን የወለደችው ጎንደር ዛሬም የወያኔን ፍፃሜ ደወል ደውላለች።”

g7

g5 g6 g8 g9 g10 G11 G12

p1