ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ

ዜና ፍኖተ ዴሞክራሲ (14 መጋቢት 14 ቀን 2008): በሰሜን ጎንደር የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላነሳው የማነነት ጥያቄ ወያኔ ትግሉን ለማኮላሸት ያደርገው ሙከራ ስላልተሳካለት ለወልቃይቱ ችግር ተጠያቂው በራሱ አምሳል የፈጠረው የወያኔው ብአዴን ነው በማለት የብአዴን መካከለኛ አመራሮቹንና ከፍተኛ ካድሬዎቹን በትግርኛ ተናጋሪ የህወሃት አባላት ለመተካት ማቀዱ ታውቋል  – በጎጃም ክፍለ ሀገር በጣና ሐይቅ ላይ በደቀ እስጢፋኖስ ገዳም ላይ የዘረፋ አደጋ እያንጃበበ መሆኑን ባህር ዳር ለሚገኙ የወያኔ ባለሥልጣናት ቢገለጽም እስከ አሁን የወሰዱት እርምጃ እንደሌለ  ተገልጿል – የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቢቀርብም የወያኔው አገልጋይ የሆነው የፍርድ ተቋም  ፖሊስ ለምርመራ የ28 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀውን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ወህኒ መልሶታል – በምዕራብ ወለጋ በመንዲ ከተማ የሚገኘው የገበያ ቦታ የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ታውቋል – የኢትዮጵያ የልማት ባንክ ለወያኔ መሪዎችና የጦር አለቆች በብድር ስም በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ካዘራፈ ወዲህ ለሰፋፊ እርሻዎች ብድር  እንዳይሰጡ ማዘዙን ባለሙያዎች ተናግረዋል – የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካፒታል እጅግ አነስተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ የወያኔ ፓርላማ የልማት ባንኩን ካፒታል ለማሳደግ ለወያኔ ፕርላማ አዲስ ህግ እንዲቀርብና የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ አገዛዙ የመድግመው ገንዘብ ስለሌለው የቦንድ ሽያጭ እንዲያደርግ ወስኗል። ይሁን እንጅ ቦንዱ ለሀገር ውስጥ ለሀገር ውጭ ቁርጥ ያለ አቋም አልወሰደም – በሕዝብ መከራ ስቃይ የግል ደስታና ምኞት ብቻ ሳይሆን ጥቅም መሰብሰብ መለያቸው የሆነው የወያኔ መሪዎች በአነስተኛ የጉሊት የንግድ ስራና በዝቅተኛ የኑሮ ደርጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከጉሊት ንግድ ማባረሩ ታወቀ – በመቀሌ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች የትግራይ ገዥዎችና የከተማው ባለሥልጣኖች ያወጡትን አዲስ የባጃጅ ሕግ በመቃወም የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ታውቋል – እስካሁን በተሰጠው የፖሊስ መግለጫ ትናንት መጋቢት 13 ቀን 2008 ዓም በቤልጅየም ዋና ከተማ በብራስልስ በአውሮፕላን ማረፊያውና በከተማው ባቡር ጣቢያ በፈነዱት ቦምቦች በጠቅላላው 34 ሰዎች የተገደሉ መሆናቸውተገልጿል- የናይጀር ፕሬዚዳንት ማማዱ ኢሱፉ በምርጫ  ያሸነፉ መሆናቸውን የአገሪቱ የምርጫ ቦርድ ገለጸ – እሁድ መጋቢት 11 ቀን በኮንጎ የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ  በተገኘው ከፊል ውጤት ላለፉት 32 ዓመታት በስልጣን ላይ የነበሩት የ72 ዓመቱ ሳሶ እንጉሶ አሸንፈዋል ተብሏል – ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓም ከብሩንዲው ፕሬዚዳንት ጋር ቅርበት እንዳላቸው የሚታወቁ አንድ የብሩንዲ ከፍተኛ የጦር መኮንን በወታደራዊ ተቋም መሥሪያ ቤት ውስጥ እንዳሉ የተገደሉ መሆናችው ተዘግቧል።  ዝርዝር ያዳምጡ ወይም ያንብቡ::