የሀገርን ደጀን ኃይል ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረገው መሯሯጥ መቆም አለበት

(ኢሕአፓ) – ኢሕአዴግና ብልጽግና፣ ኦሕዴድ እና ኦዴፓ እንዲሁም ብአዴንና አዴፓ ምንም ልዩነት የሌላቸው ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻዎች እንደሆኑ ኢሕአፓ ደጋግሞ መግለጹ ይታወቃል። አሸባሪው የወያኔ ቡድን ገና ቀብሩ ባልተጠናቀቀበት እንዲያውም ከባድ ሽንፈት የገጠመውን ታጣቂ ኃይሉን አሰባስቦ በአፋር፣ በወልቃይት፣ በጠለምት እና በራያም ሕዝብ እየገደለና እያፈናቀለ፣ ንብረት እየዘረፈና እያወደመ በቀጠለበት ሁኔታ ቀደም ብሎ የሽብር ቡድኑን ድባቅ ተመትቶ እንዲያፈገፍግ በተደረጉት ፍልሚያዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገውን የፋኖን ሕዝባዊ ኃይል ኢመደበኛ አደረጃጀት ነው በሚል ሽፋን ትጥቁን ለማስፈታትና ለመበታተን በአገዛዙ በኩል የተደረገው ውሳኔ በከፍተኛ ደረጃ የሚወገዝ ወንጀል ነው። ይህ እርምጃ አገዛዙ በወገንና በአገር ላይ ያለው ንቀት እና ጭካኔ እስከምን ድረስ የዘለቀ መሆኑን የሚጠቁም ሲሆን ሕዝብን በቋንቋና በዘር ከፋፍሎ የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሸረበው ሴራ መሆኑን ያሳያል። የተዳከመው የወያኔ ቡድን ህልውና ኖሮት መቆየቱ የሥልጣን ዕድሜየን ያራዝምልኛል ብሎ የሚያምነው የብልጽግና አገዛዝ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የወሰነው ለወያኔ ቡድን የህልውና ስጋት እንዳይሆን ነው ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም። የወያኔ ቡድን ቀደም ብሎ ከወረራቸው ቦታዎች ድባቅ ተመትቶ ሲያፈገፍግ ጨርሶ ሊወድም የሚችልበትን አጋጣሚ ለማሰናከል የወገን ኃይል ወደ ትግራይ እንዳይገባ የተደረገበት ውሳኔ፣ የወያኔ ቀንደኛ መሪዎች እነስብሓት ነጋ በሕገ ወጥ መንገድ የተፈቱበት ሁኔታ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በጀርባ ከወያኔ ጋር የሚያካሄዱት ድርድሮች ፋኖን ትጥቅ ከማስፈታትና ከመበታተን ሴራ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው። ሙሉውን መግለጫ . . .