የልዴቱን ሰላይነት፣ የዓላሙዲንን ዘረፋ የሚያጋልጠው መደመጥ ያለበት ቃለ ምልልስ

ከዓመታት ቀደም ሲል ጀምሮ፣ ልዴቱ አያሌው በተቃዋሚው  ጎራ  የተተከለ የወያኔ  ሰላይ መሆኑን  በመግለጽ  አፍቃሪ ኢሕአፓ  የሆኑ  የተለያዩ ጋዜጦች፣ ድረገጾችና  የማህበራዊ መገናኛዎች የሚከሱት  መሆኑ  ይታወሳል።  የወያኔንና  የምዕራባዊያን አማካሪዎቹን የረቀቀ ተንኮልና አፈና  ልብ ያላሉ ብዙ የዋሃንም ይህንኑ ማስጠንቀቂያ  ቸል ሲሉት፣ አንዳንዶቹም የልዴቱ ተከራካሪና  ደጋፊ ሆነው ሲጭበረበሩለት ታዝበናል። ነገሩ ቆቅ ለቆቅ ነበረና ለካ፣ በወያኔ  የደህንነት መስሪያቤት ውስጥ፣ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣  የካርጎ  ተርሚናል የደህንነት ሃላፊነትን ጨምሮ በተለያዩ  ከፍተኛ  የስልጣን እርከኖች ያገለገሉ  አንድ ሰው በቅርቡ ባደረጉት  ቃለመጠይቅ ይህንኑ አረጋግጠዋል።  ልዴቱ በወያኔ  ተቀጥሮ  የሚሰራ ስለመሆኑ ሲናገሩ:

“  . . . . በሽግግሩ ወቅት እንደውም የህወሃት የወጣት ፎረም አባል ነበር። ከዚያ ነው የሚጀምረው። ከዚያም በሁዋላ በደህንነቱ ውስጥ በነዳጅ ማደያው አካባቢ በሚገኝ አካል  ይሰራ ነበር። ያ ነዳጅ ማዳያ  ያለው አሁን የስደተኞ እና የስደት ተመላሾች ጉዳይ ዋና መምሪያ ያለበት ማለት ነው።  እሱ መጀመሪያ  የተመለመለው የኢሕአፓን አባላት እንዲከታተል ነው። … ”  በማለት ጀምረው፣   በተደጋጋሚ የኢሕአፓ  አባላት/ደጋፊዎች ከዚህ በፊት ይሉት የነበረውን ክስ እራስ አወቅ ማስረጃ (ፈርስት  ሃንድ ኢንፎርሜሽን) በማቅረብ እውነት መሆኑን ገልጸዋል። የዶ/ር ኃይሉ ዓረአያንም ጭምር። የወያኔ  አገዛዝ  ዋና  ደጓሚ  ስለሆነው የሳዑዲው ባለገንዘብ ዓላሙዲም  ዘረፋና  ወንጀል ተናግረዋል።  መታየት ያለበት  ቃለመጠይቅ።

 

https://www.youtube.com/watch?v=5K5bKaYev2M