የመምህራንና የሌላው ሕብረተሰብ ትግል ተጠናክሮ መቀጠል የወቅቱ ጥሪ ነው

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ:  . . . ሰሞኑን … በ33 ት/ቤቶች የሚያስተምሩ የደሴ ከተማ መምህራን ውስጥ ውስጡን ሲነጋገሩና ሲወያዩ ከቆዩ በኋላ ሚያዝያ 14 ቀን 2008ዓ.ም በተካሄደው አጠቃላይ የመምህራን ማህበር ስብሰባ ላይ ጥያቄዎቻቸውን ጠንከር ባለ መልኩ ለሚመለከተው ክፍል አቅርበዋል። ለጥያቄዎቻቸው አፋጣኝ መልስ የማይገኝ ከሆነ የስራ ማቆም አድማ የሚያደርጉ መሆናቸውንም በአቋም መግለጫ ውስጥ በማስፈር በየት/ቤቱ በሚገኙ መሰረታዊ መምህራን ማህበር ተወካዮች አማካኝነት ፔትሽን ተፈራርመው ልከዋል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ