የመምህራን ጩኻት – እንደመምህርት መሰሉ መንጋው ላለሞት ትግሉ ተፋፍሞ ይቀጥል

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ – ከሞቱት መኸል የብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪ መምህርት መሰሉ መንጋው፣ ባላቤቷና ሶስት ልጆቿዋ ሕይወታቸው አልፏል። ለመምህርት መሰሉ መንጋው፣ ለቤተሰቦችዋ፣ እንዲሁም በዚህ አስቃቂ ሁኔታ ለሞቱት ወገኖቻችን በሙሉ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባበሪ ኮሚቴ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል። ለቤተሰቦቻቸውም እግዚአብሔር ጽናቱን እንዲሰጣቸው ይመኛል።  እነዚህ ወገኖቻችን ቆሻሻ አካባቢ ኖረው፣ ቆሻሻ ተመግበው፣ ቆሻሻ ተንዶባቸው ላንዴና ለመጨራሻ አሸልበዋል። ባንጻሩ ትናንት በባዶ እጅ ወደ አዲስ አበባና የተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የገቡት የወያኔ ባለሥልጣናት ዛሬ ቢሊንየርና የባለብዙ ፎቆች ባላቤት ሆነዋል። ሙሉውን ያንብቡ