የሾላ ዛፍ ማፍራት የጠቀመው ለአዕዋፍ ነው፣ ዛፉ አልተጠቀመም!

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ሐተታ፡ በኢትዮጵያ ሕዝብ የረዥም ዘመናት ታሪክ ሂደት፤ ገናና የታሪክ ምዕራፍ አስመዝግቦ አልፏል የተባለለት፤ የየካቲት ወር 1966 ዓመት ምህረት ዐብዮት ነበር።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐብዮት!  ኢትዮጵያዊ ዐብዮት ነበረ!  ያልተዳቀለ፤ ያልተበረዘ፤ ያልተዘነቀ፤ ያልተበወዘ፤ ያልተለወሰ ያልተደረተ፤ ወጥ (ኦርጂናል) የሆነ ኢትዮጵያዊ ዐብዮት ነበር።  የኢትዮጵያም ሕዝብ አንጡራ ዐብዮት ነበር።  እንደ ሸቀጥ ዕቃ ከውጭ ያልገባ! ከኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ ተርግዞ፤ ከኢትዮጵያ ማህፀን የተወለደ ኢትዮጵያዊ ዐብዮት ነበር።  ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …