የተዳፈነ እሳት የጠፋ ይመስላል:: በኢሕአፓ ላይ ዘመቻው ተጧጧፈሳ!

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጵ ሬዲዮ ሀተታ (ክፍል 1): በቅርቡ ወደ አሜሪካ ተጉዞ በዚያ ትውልድና በኢሕአፓ ላይ ጸያፍ ዘመቻ የከፈተው የቆሻሻ ታሪክ ባለቤት ፕሮፌሰር እንጂ ደርግ 60 ዎቹ ላይ ላደረሰው ግድያ ኢሕአፓ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። የአሜሪካ መሳሪያ ሆኖ አልተገኘም። የደርግ ኢሰፓ ባለስልጣን ሆኖ ግፍ በሕዝብ ላይ አልፈጸመም። በአሶሳ ሻዕቢያና ኦነግ አማራውን ሲገድሉ ዝም አላለም፤ አወገዝ አጋለጠ እንጂ። በከተማ በገጠር ደሙን ለሀገሩ አፈሰሰ እንጂ በደርግ ለነጻ ትምህርት በየኩባና ምስራቅ አውሮጳ አልተላከም። ኢሕአፓ ለሀቅ ቆመ እንጂ በሬ ወለደ፤ በመውለድ ላይ ነው ይወልዳልም ከሚሉ ነፍሰ ገዳዮችና አረመኔ አገዛዞች ጋር አልሰመረም፤ አላበረም። ምናልባትም ይህ ይሆናል አላቋርጥ ላለው የሀሰት ዘመቻ ምክንያት የሆነው። ሙሉውን ያንብቡ