የተፋፋመውን ህዝባዊ ትግል ተከትሎ በተፈጠረ ፍርሃት በአዲስ አበባና አካባቢዋ የቤት ዋጋ እያሽቆለቆለ ነው

የወያኔን  የሃያ አምስት ዓመት ከፋፋይ ሰንሰለት እየበጣጠሰ እና የተጫነበትን የእመቃ ዘረኛ አገዛዝ 199እየታገለ ያለው ሀገር አቀፍ ህዝባዊ የተቃውሞ  እንቅስቃሴ  በፈጠረው ፍርሃት ሰበብ በአዲስ አበባ እና  አካባቢዋ የቤት እና የቦታ ዋጋ በፈጣን ሁኔታ እያሽቆለቆለ  ነው።   ከወያኔ ጋር ያላቸውን  የደም ፣ የአምቻ  ጋብቻ ቅርርብ በመጠቀም፣ ወይም ህሊናቸውን  ሸጠው የፖለቲካ  ታማኝነት በማትረፍ፣ ሌሎች ዜጎችን  በሃይል በማፈናቀል፣ እንዲሁም ተገቢ ባልሆነ  አሰራር ከባንክ እየተበደሩ፣ የቤት እና የቦታ ባለቤት  የሆኑ  ብዙ ሰዎች የጀመሯቸውን ቤቶች እስካሁን ያወጡትን  ገንዘብ ከፍሎም  ቢሆን የሚጋዛቸው  አጥተው ሲቸገሩ ይስተዋላል።  ከጥቂት ወራት በፊት 1 ስኩዬር  ሜትር  ቦታ በ31, 110 ብር ሂሳብ  ይሸጥባት በነበረችው  በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ፣ የቤት ዋጋ ምን ያህል እንደወረደ ማሳያ ይሆኑ ዘንድ:
_  በከተማዋ አንደ ሶስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ያለቀ  ቤት  በ900 ሺህ የኢትዮጵ ያ ብር (40 ሺህ 909 የአሜሪካ ዶላር) ዋጋ  ሊሸጥ  ማስታወቂያ  ወጥቶበታል። ገዢ በዛብኝ ካለም የተጠቀሰው ዋጋ ላይ ሊደራደር መቻሉ  በማስታወቂያው  ላይ  ተጠቅሷል፣
_  በአዲስ  አበባ ዳርቻም አንድ ባለ 1 ክፍል ሳሎን፣ 2 የመኝታ ክፍል፣ 2 የምግብ ክፍል፣ 2 የመታጠቢያ ክፍል እና ከ 2 እስከ 3  መኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው የተገባደደ ቤት በ500 ሺህ ዋጋ  (22 ሺህ 727 የአሜሪካ ዶላር)ለሽያጭ  ቀርቧል።  የዚህም ቤት ባለቤት ቢሆን የተጠሰው ዋጋ ለድርድር  ክፍት መሆኑን  ገልጹዋል።
ዱሮውንም ወያኔዎች እራሳቸው ፖሊሲ አውጭ፣ እራሳቸው ፖሊሲ ተግባሪ፣ እራሳቸው ተቆጣጣሪ፣ እራሳቸው አበዳሪ፣ እራሳቸው ተበዳሪ፣ እራሳቸው ቤት ሰሪ፣ እራሳቸው ቤት ሻጭ በመሆን  በሙስናና በአድሎዎ አጡዘውት የነበረው የቤት ዋጋ የጀመረው የቁልቁለት ጉዞ እንደሚቀጥል ግልጽ ነው።
ከላይ በምሳሌነት የተገለጹት ቤቶችን ዋጋ እንደተመለከተው ከተማ ውስጥ ያለው በአሜሪካ  ዶላር 40 ሺህ ያህል ነው፣  ከተማ ዳርቻ ያለው ደግሞ 22 ሺህ ዶላር። ዘረኛነት እና  በቃኝን የማያውቅ ስግብግብነት  የመለያ  ባህሪው የሆነው  ወያኔ፣ ከጥቂት ሳምንት በፊት  በውጭ  ከሚኖሩት ውስጥ የተወሰኑ  የአማራ  ተወላጆችን ባህርዳር ላይ ሰብስቦ፣ በየትውልድ አካባቢያቸው ቦታ  እንዲመሩ ሲሰብክ፣ በመጀመሪያ  ክፍያነት 20 ሺህ የአሜሪካ  ዶላር  ከፍለው ለዘረፋ  ወደ አዘጋጀው ካዝና እንዲያሰገቡ የተጠየቁት ገንዘብ፣ በአዲስ አበባ  አካባቢ አንድ ቤት ሊገዛ  መቃረቡን ልብ ሊሉት  ይገባል።  በመስመጥ  ላይ ላለ  አገዛዝ ለፍተው ያገኙትን ገንዘብ በመስጠት፣ ባዶ  እጃቸውን እንዳይቀሩ፣  የራሳቸውን ወገን ለመግደልና ለማፈን ጥቅም ላይ የሚያገለግል መሳሪያ  ከውጭ  ለመግዛት አገዛዙ የሚጠቀምበት የውጭ  ምንዛሬ እንዳይሰጡም መጠንቀቅ አለባቸው።  በወንጀል በጨቀየው የወያኔ  ፍርፋሪ መነካካት ከህሊናም አልፎ  ነገ  የፍትህ ጥያቄም ሊያስከትል ይችላል።