የአማራ ሕዝብ የመቅሰፍት አደጋ አንዣቦበታል!

 

ኢሕአፓ፡ የወያኔ አገዛዝ በአሁኑ ወቅት እየተውተረተረ ያለ በመሆኑ ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻ በ 2007 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው "ሕዝባዊ ምርጫ“ ለድጋፍ ማግኛ መጠቀሚያ ለማድረግ እየጣረ ነውና የተቃጣው አደጋ እውንና የምርም ነው። ማንም ለኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገሪቷ ቀናኢ የሆነ ሀገር ወዳድ ሁሉ በቸልታ ሊመለከተው የማይገባው ነው። በመሆኑም ኢሕአፓ የአማራን ሕዝብና ሁሉ አቀፍ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ኃይሎች እያንዣበበ ካለው የጥፋት ሴራ ራሳቸውን እንዲከላከሉና የዘር ማጥፋት ተግባር፤ ጥላቻና፤ በአማራው ላይ የተቃጣውን የግድያ ዘመቻ አጥብቀው እንዲቃወሙ ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …