የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋጋታ፤ የሕዝቡን ዐመፅ አይገታውም! በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀው ጦርነት ብርቱ ተቃውሞ ገጥሞታል!

በፍኖተ ዴሞክራሲ   የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ – የሀገራችን ሕዝብ ለአለፉት ሃያ ስድስት ዐመታት የተጫነበትን አንገፍጋፊ ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም ከዳር እስከዳር ወሳኝ ትግል እያከሄደ፤ አይከፍሉ መሥዋዕት  ሲከፍል ቆይቷል።  በርካታ የሕዝብ ወገኖች፤ ሀገር ወዳድ ታጋዮች፤ የኅሊና  እስረኞች፤ የሃይማኖት አባቶች፤ ወጣቶችና አዛውንት መሥዋዕት በመክፈል፤ ሁሉም  ግዴታቸውን ተወጥተዋል።   የሀገርና የወገን ፍቅር ውድ ዋጋ እንደሚያስከፍል በተግባር አስመስክረዋል።   መዳረሻቸው  በትክክል የልታወቀ የሀገሪቱ ብርቅ ልጆች  አስታዋሽ አጥተው ቀርተዋል።   ፍለጋው ግን እንደቀጠለ ነው።  የእነርሱ ሁነኛ መዳረሻ እስከልታወቀ ድረስ  ትግሉ  አይቆምም።  ሙሉውን  ሀተታ ያንብቡ