የአንድን ትውልድ ታሪክ መግደል፤ ሀገርን እንደ መግደል ይቆጠራል

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (ህዳር 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የተላለፈ):  ሀገር ማለት፤ ሜዳው ሸንተረሩ፤ ጫካና ሸለቆው፤ ወንዙና ባህሩ ብቻ ሳይሆን ፤ በውስጡ የሚኖሩትን ሕዝቦችንም ያቀፈ መልከዐ ምድርም ጭምር ነው።  ሀገርን፤ ሀገር ብሎ ለመጥራት ከተፈለገ፤ በውስጡ የሚኖሩ ሰዎች እንዲኖሩ የግድ ይሆናል።  ያለ ሕዝቦች ሀገር የሚባል ነገር አይኖርም።  ሀገር የሚባለው ፤ በውስጡ ዜጎችን አቅፎ በመያዙ እንጅ፤ ዜጎች ከሌሉበትማ ምድረበዳ ከመባል በስተቀር፤ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።  ይህ ሀቅ፤ ተፈጥሮና ታሪክ የሰጡት መሠረታዊ ትርጉም አለው።   ሕዝብ የሌለበት መልከዐ- ምድር ሀገር ሊባል አይችልም፡፡  በመሆኑም፤ ምድረበዳ ተብሎ ከመጠራት አይዘልም።  ሰሓራ በረሃ፤ ጎቢ በረሃና ካላሃሪ በረሃ፤ ሁሉም ምድረ በዳዎች ናቸው። ሰው ሰለማይኖርባቸው ፤ ሀገሮች ተበለው አይጠሩም።  ምድረበዳዎች፤ በረሃዎች (Deserts) ተብለው ነው የሚጠሩት።  ሕዝብ፤ የሀገር ማዕካላዊና ዓይነተኛ መሠረት ነው።  ሕዝብ ሳይኖር፤ ሀገር አለ ቢባል፤ የቅኝ ግዛትን ለማስፋፋት ከሚደረግ የቅኝ ገዢዎች አስተሳሰብ የተለየ ሊሆን አይችልም።  ቅኝ ገዥዎች፤ ፍላጎታቸው የሚወሩትን ሀገር እንጅ፤ ነዋሪው ሕዝብ ቢጠፋ ባይጠፋ ደንታ አይሰጣቸውም።  ሙሉውን ያንብቡ…