የኢመማ ጀግኖች ሰማእታትን እናስብ

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ፡ የዛሬ 17 ዓመት ሚያዚያ 30 ቀን 1989 ዓ.ም አቶ አስፋ ማሩ ከቤቱ በሰላም ወጥቶ ወደ ሥራ በመሔድ ላይ እያለ በአዲስ አበባ ሐምሌ19 የሕዝብ መነፈሸ አካባቢ በጠራራ ጸሐይ በወያኔ/ኢህአዴግ ነፍሰ ገዳይ ፖሊሶች የጥይት እሩምታ ሰለባ የሆነ ጀግና ኢትዮጵያዊ ነው። … አቶ ሺመልስ ዘውዴ በወያኔ/ኢህአዴግ ፖሊስ ጣቢያ ለአንድ ወር ያህል ታስሮ በነበረበት ጊዜ ለከፋ ብርድ ሕመም በመጋለጡ፣ ሕክምና ባለመግኘቱና በደረሰበት እንግልት ከእስር ከተፈታ በኋላ ወዲያውኑ ሕይወቱ አልፏል። አቶ ከበደ ደስታ በኢመማ ሥር የአባት መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩትም ታሰረው ሕይወታቸው እስር ቤት እንዳሉ አልፏል። እቶ አወቀ ሙሉጌታ የኢመማ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና በጥንካሬው የምናደንቀው የኢመማን ጽ/ቤት ለተላጣፊ ለአለመስጠት የሙጥኝ እንዳለ አሟሟቱ በግልፅ ሳይታወቅ በመጋቢት ወር 1999ዓ.ም መንገድ ላይ ሞቶ ተገኝቷል። አቶ ሰርዶ ቶላ፣አቶ ፈቃዱ ፍርዴና ሌሎችም ኢመማ ካፈራቸውና በዕምነነታቸው ጸንተው ካለፉት ጀግኖች ቀዳሚዎች ናቸው። በቅርቡ በሕዳር ወር 2004ዓ.ም ደግሞ ፍትሕ በሌለበት አገር መኖር ባዶ ሕይወት ነው በማለት ራሱን በጋዝ አንድዶ መስዋዕት የሆነው መምህር የኔ ሰው ገብሬ ቆራጥነቱ ሕዝቡን ያስደመመ ሆኖ አልፏል።  ሙሉውን ያንብቡ...