የካቲት 1966 — ድገመና!

ዴሞክራሲያ (ቅፅ 41 ቁ. 5 የካቲት 2008 ዓ.ም.) – የካቲት 66 አብዮት ከተከሰተ 42 ዓመታት አልፈዋል።  የኅብረተሰብ ሂደት ሆነ እድገት አንድ ወጥ አይደለምና በዚህ ረጅም ጊዜ ሀገራችን ብዙ ለውጦችን አሳይታለች።  በዚያውም ልክ መከራዋና ችግሯ፤ ህመሟና ቅጥቃጤዎቿ አሁንም እንደቀጠሉ አሉ። ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ወደ መቶ ሚሊዮን ተጠግቷል፤ አብዛኞቹም ወጣቶችና ሴቶች ናቸው።  ዘመን ተለውጦ የአካባቢውና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ እንደቀድሞው አይደለም። የዚህ ሁሉ አንደምታ እንዳለ ሆኖ ግን የየካቲት 66 መሠረታዊ መንስዔዎች ዛሬም ወቅታዊነትን እያንጸባረቁ አሉ።  ሙሉውን ያንብቡ …