የወያኔን ብሎን ለማወላለቅ

ብሎኖቹ ሁሉ የወላለቁ፤ የተበላሹ፤ ቤንዚን አልባ የሆነ መኪና ሊንቀሳቀስ አይችልም ነው። ወያኔም እንደዚያው ነው። የአፈና መሳሪያዎች ስላሉት ብቻ በሰላም ሊገዛ አይችልም። የአፈና መሳሪያዎቹን ራሳቸውን ማበለሻሸት፤ ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይቻላል። የደርግን ግዙፍ ጦር ውድቀት ያጤኗል!  ወያኔ መንግስት ሆኛለሁ ብሎ ሲውገረገር ከመቀሌ እስክ ሞያሌ፤ ከጅማ እስከ አሳይታ መዋቅር ዘርግቻለሁ ባይ ነው። ለዚህ ስራው በመለስተኛ ቡችላነት፤ ባርነት የሚያገለግሉትና ሕዝብን በጎሳና በሀይማኖት ከፍለውለት የሚሰሩለት አሉ። ተለጣፊና ቅጥረኛ የምንላቸው እነ አዲሱ-ብአዴን፤ እነ ሀይለማርያምና አባዱላ ዓይነቶቹን ማለት ነው። የወያኔ መዋቅር ወልገድ ወልገድገድ ካለ ቆይቷል። ሙስናና ዘረኝነት እንደ ምስጥ በልቶታል። አውራጃዊነት ምርጥ ዜጋ የተባሉትንም እያመሳቸው ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መብታችን እምነታችን ይከበር ብለው ትግል ከጀመሩ ዓመቶችን እያስቆጠሩ ነው። ሕዝብ እንደ ህዝብ ቅሬታ ይዟል፤ ከባድ ቂም ቋጥሯል። ሂሳብ ማወራረጃ ቀንን እየጠበቀ እንዳለም ግልጽ አድርጓል ማለት ይቻላል።  ሙሉውን ያንብቡ…