የወያኔ አገዛዝ–አደገኛ የቆሻሻ ክምር

(የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ሀተታ)

መብታችን ይከበር ብለው ወያኔን ተቃውመው የተነሱት ሁሉ ደማቸውን አፍሰው ይህን የገማ የገለማ ዘረኛ አገዛዝ እንዳጋለጡት ሁሉ፣ በሰሞኑ የቆሻሻ ናዳ የገደላቸውና የቀበራቸው  በርካታ ዜጎች ደግሞ የወያኔ አገዛዝ ምን ያህል ዋሾ፤ ፍትህ አልባ፤ ዘረኛና በዝባዥ–እንዲሁም ህሊና ቢስ–መሆኑን ለዓለም አጋልጠዋል።

ኢትዮጵያ በኤኮኖሚ አደገች ተመነደገች፤ ቻይናን ልታስንቅ ተቃረበች እየተባለ የሚለፈፈው ሁሉ ለወያኔ ባለስልጣኖችና ለባዕዳን ደጋፊዎቻቸው  ብቻ  የሚታይ፣  ሀቅ ግን ሌላ መሆኑን ዓለም እንዲገነዘብ ሆኗል። ባዕዳንማ ሎሌ አገዛዝ አግኝተዋልና ማመስገን የሚጠበቅባቸው ነው። ስለ አፍሪካ ሁኔታ ምንም የማያውቀው አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ ወያኔን አወድሶ፤ እርዳታ ይሰጠው ብሎም መማጸኑ ምንኛ ነጮቹ ኢትዮጵያን ሊጎዱ እንደተነሱ የሚያስረዳ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ረሃብ ሰፈነ ሲሉ ሚሊዮኖች በቀጣይ ረሀብ የሚሰቃዩባትን ሀገር መጥቀስ አለመፈለጋቸውንም  ታዝበናል። ዜጎች ከገማ ቆሻሻ ክምር ስርና ዙሪያ እየኖሩ፣ ምግባቸውን ከቆሻሻው የሚያገኙ ከሆነ፤ ይህች አገር ሆነ ከተማ አደገች ሊባል ከቶም  የሚቻል አይደለም። ከግማሽ ሚሊዮን ሰው በላይ–በአብዛኛው ህጻናትና ሴቶች–መንገድ ላይ እያደሩ ባለበት ስለ ዕድገት ማውራት በሕዝብ ቁስል ላይ ጨው መነስነስ ነው።

ዕድገት ማለት ብዙሃኑ ከችግርና ድህነት ሲላቀቅ እንጂ ጥቂት ዘረኞች ተንፈራጠው ሀገርን ሲግጡ አይደለም።  ሚሊዮኖች  ተርበውና ታርዘው ባለበት ጥቂት ጨካኞች ዘመናዊ ሆቴሎችን ከፍተውና በሙስና ተጨማልቀው ስለከበሩ አይደለም። ውሃና መብራት የሌለው፤ የገማ ኮንዶሚኒየም ተብዬን ሸጦ ለጥቂቶች ኪስ ማዳለብያ ማዋል አይደለም። ያውም ነገ መሬት ቢንቀጠቀጥ ለሚንኮታኮት በኮሾ ስሚንቶ ለተሰራ ህንጻ። የኤኮኖሚ እድገት ማለት ጥቂቶችን አበልጽጎ የብዙሃኑ አለፈላቸውን ልብወለድ ውልዶ ከዕለም ሀገሮች ውስጥ ከነጡት፣ ከተሰቃዩት ድሃ ሀገሮች አንዱ መሆን አይደለም። በሁሉም መስክ ሲመረመር የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ዕድገት ወያኔን ለመጥቀም የተደወረ የዓይን አውጣ ውሸት መሆኑ ግልጽ ነው። ቅንጣትም ለሕዝብ የማይፈይዱ አፍሪካኖች ነጭ ዝሆን የሚሏቸውን የጉራ ዕቅዶች እያናፈሰ ያለው ወያኔ የጉቦ ጥሙን ያረካል እንጂ የአስገኘው ጥቅም የለም። ስንትና ስንት ግድቦች በስንት ቢሊዮን ብር ተገንብተው ለሕዝብ ምንም አልጠቀሙም።  የአባይን ግድብ ቦንድ ወያኔ በላው በተባለው መሰረት ሰራተኞች ደሞዝ ሳይከፈላቸው ወራት አልፈው፤ ሲቃወሙ አፈና እየደረሰባቸው ይህ ግድብ እንኳን በዚህ ዓመት ቀርቶ በመጪዎቹም እንዳማያልቅ ውስጥ አዋቂዎች ተላሎችን አስረድተዋል። ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጥቀም ምንም እርምጃ እንደማይወስድ የሚታወቅ ነው። ከ 480 ሚሊዮን ዶላር በላይ አወጣ የተባለውና ለቻይና የጠቀመው አንድ አውቶቡስ የምታክለው የከተማ ባቡርስ ምን ደረሰባት? ወያኔ አገልጋያችን ነው ባዮቹ ባዕዳን ሀገሮች ገበናውን ሸፍነው እንድሚንከባከቡት ከታወቀ ጊዜ አልፏል። መሬታችንን የሚበዘብዙት ቻይና፤ ሳውዲ፤ ወዘተ ለምንስ ብለው ወያኔን ይውቀሱ፤ ለምስን ብለው የዚህን አገዛዝ ተራ የቆሻሻ ስብስብና ክምርነት ያጋልጡ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንም ጠበቃና ተካላካይ ሳይሆነው ከ 25 ዓመት በላይ ሲሰቃይ ቆይቶ በ ከእንግዲህ መብቴን ላስከብር ብሎ የተነሳውና መስዋዕትነትንም እየከፈለ ያለው አለምክንያት አይደለም። በዚሁ ልክ ባዕዳን የሕዝብን ትግል ለማፈን ቅጥረኞቻችውን ታጋይ አስመስለው ማሰማራታቸውንም ሳንታዘብ አልቀረንም።

ኢትዮጵያ ታታሪ ሕዝብና ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት እያላት የድሃ ድሃ መሆኗ በጣም የሚጸጽት ነው።  ላስቲክ ጫማ አድርገው ሞገውና ከስተው ተርበው ለአዲስ አበባ የበቁ የችጋር ምሳሌዎች ሳይውል ሳያድር እንደተራበ  ጅብ ኢትዮጵያን ቦጭቀው ወፈሩ፤ ፈንጂ ቦርጭን ያዙ፤ አሳዩ፤ ሚሊዮኖችን በሀገርም በውጭም በባንክ አካበቱ፤ ሕዝብን ከመሬቱ አፈናቅለው ራሳቸው ነጠቁ፤ ለባዕዳንም በርካሽ ቸበቸቡ። ሕዝብ ተደራጅቶ እንዳይታገላቸው የሕዝብን ማህበራት በሞላ በሀይል አፈረሱ። ይታገለናል ባሉት ሕዝብ ላይም ይህ ነው የማይባል አፈናና ግፍ ፈጸሙ። የሕዝብ መሪዎችን አገቱ ገደሉ።  የሰብዓዊ መብትን ደብዛ አጠፉ።  ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ቢያንስ በ 11 በመቶ በየዓመቱ አደገ እያሉ ሲለፍፉ ሁሉም ነገር ምትሃትና ላም አለኝ በሰማይ የሆነበት ህዝብ ግን በኑሮ ውድነት ደቆ፤ ተርቦ፤ እንኳን የገዢውን መደብ ሙክት ፍየል ሊበላ ከሆቴሎች በሚመጣ ትርፍራፊ–ያውም ከቀናው– ሆዱን ሊሞላ ሞክሮ ድህነቱን ተላብሶ እስከዛሬ አለ።  የምን ዕድገት? በቆሻሻ ናዳ የሞቱት በርካታ ወገኖች የወያኔ አገዛዝ ዋና ትሩፋቶች ናቸው። ያለው አሰቃቂ ድህነት ምሳሌዎች፤ መረጃዎች። ወያኔ ወደ ሌላ ቦታ የተረፉትን ውስጄ አሰፍራለሁ ያለውም ያው የተለመደ ቅጥፈቱ ከመሆኑ ሌላ በዚህ አሳቦ መሬት ነጠቃ ሊገባ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። እስከዛሬ ሳያያቸውና ስቃያቸውን ሳያቅ ቀርቶ ነው? እውን ሀገር ወዳድ መንግስት ቢኖር ኖሮ ኢትዮጵያውያን ክቆሻሻ ምግብ እየፈለጉና እየለቀሙ ሊኖሩ ተገድዋል ማለት በጣም የሚያሳፍር መሆኑን ማንም አይስተውም። ወያኔና ቁንጮዎቹ ኢትዮጵያን አጥብቀው ስለሚጠሉ ሀገራችን ስትዋረድ፤ ሕዝባችን ሲሰቃይ ከበሮ ይደልቃሉ እንጂ የሚያዝኑ አይደሉም። ለእኛ የኢትዮጵያ መንግሥት የለም። ጨካኝ አገዛዝ ግን እውን ከሆነብን ዓመታት አልፈዋል። በስልጣን ያለው የቆሻሻ ክምርና ስብስብ ጸረ ኢትዮጵያ ጸረ ሕዝብ ነው። ለዚህም ነው ለወያኔ ምንም ምህረት የማያስፈልገው ። ይህ ግዙፍ በደል ያልነካቸው፤ ያልተሰማቸው ህሊና ቢሶችና ሆድ አምልኪዎች ግን ወያኔ የሀገር ታዳጊ የሆን አስመስለው ሊወያዩት፤ ሊያብሩት፤ ስልጣኑንም ሊያራዝሙለት ማለትም ኢትዮጵያን ከወያኔ ጋር ሆነው ሊግጡ አቆብቅበዋል። ሲያምራችሁ ይቅር ለማለት ሕዝባዊ አመጹና ትግሉን ከማፋፋም ሌላ መፍትሔ የለውም።

በየቆሻሻው ቦታ ጠኔ እንዳጠቃቸው ያሉትና የሚሞቱት ዜጎች–በተለይ ሕጻናት–የወያኔን አገዛዝ ያወግዛሉ። ሞታቸው በወያኔ ላይ ከባድ ክስ ነው። መጠጊያ ቤት ኖሯቸው፤ ራቁታቸውን መሄድ ማደር ሳይገደዱ፤ በቂ ምግብ በልተው፤ እንደ ወያኔ ልጆች ወደ ውድ የውጭ ሀገር ትምህርት ቤቶች ባይላኩም በሀገራቸው የትምህርት ገበታ ተካፋይ ሆነው፤ የሕጻናትን ሳቅ ስቀውና ከሚያሳቅቅ ኑሮ ተላቀው መገኘት ሲገባቸው ሀገራቸው ሲኦል የሆነችባቸው ሕጻናት በሞላ ወያኔን ያወግዛሉ፤ ይኮንናሉ። የበላች ብትዘፍን ያልበላች ታዝን ነውና ወያኔና ጭፍሮቹ የተንደላቀቀ ኑሮ መኖራቸው ለሚሊዮኖች ያለው ትርፍ ጸጸትና ፍዳ ብቻ ነው። አዜብ፤ ሳሞራ፤ ስብሓት፤ አባይ፤ ስዩም፤ አባዱላ፤ አዲሱ፤ በረከት ብለን ከነተለጣፊዎቻቸው ሰው በላዎቹን ብንቆጥራቸው ከመቶ ሚሊዮን ሕዝብ አንጻር ኢምንት ናቸው። የአፈናውን ተቋምና የሃገራችንን ሀበት ስለያዙ ግን የገዘፉ መስለው ይታያሉ። ባለፉት ወራት በጎንደር፤ጎጃም ወዘተ በተነሳው ዓመጽ ግን ልካቸው ተገምቷል። ቡከን መሆናቸውም ገሃድ ወጥቷል። ዘረኝነታቸውን አስፋፍተው በተለይ የትግራይን ሕዝብ ከጎናቸው ሊያሰልፉ የጣሩትም በአብላጫው ውድቅ ሆኖባቸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀው አፈናና እመቃን መሳሪያቸው ማድረጋቸው ብልጠት ጥንካሬን ሳይሆን ውድቀት መጋለጥን ያሳይና እያሳየም ያለ ነው። ይህን ክደው ከትርፍራፊው ለመቀራመት የወያኔ አዳናቂና ደጋፊ የሆኑ ዜጎችና ዜግነትም የቀየሩት አደብ እንዲገዙ፤ ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ እንዳይሆኑ ስንመክር ቆይተናል። አሁንም ለተለጣፊው መንጋ ሁሉ፤ ለሆድ አደሮች ሁሉ፤ በወያኔ ጦር፤ ፖሊስና አፈና ተቋም ያሉትን ሁሉ ከዘረኛው ቡድን ርቀው ከህዝብ ጎራ በጊዜ ቢደባለቁ ያዋጣል በሚል መምከራችንን ቀጥለናል። የትግራይ ተወላጆች በተለይ የዚህ አጥፊ ቡድን መጠቀሚያ እንዳይሆኑ፤ ታሪክ እንዳይበላሽና የከፋ ነገር እንዳይመጣ እንዲጠነቀቁ አበክረን እናሳስባለን። የወያኔ መንገድ መቅሰፍትን ያመጣል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ እኮ ነው በሚል ለበጣ ይህ የሚወገድ አይሆንም። ወያኔ ሊያፈርሰው በቃጣው ዋልድባም አንዳንዴ ይዘፈናል ተብሏልና አይሆንምን ብልጠት ሰበካውን ትቶ ይሆናልን ይዞ እንዳይሆን ከህዝብ ጎን መቆሙ የተሻለ ይሆናል። ምከረው ምከረው ካልሰማ መከራ ይምከረው ማለቱን አንዳንዴ ማሰቡ መልካም ነው።

ሕንጻ፣ ቀለበት መንገድ፤ ዋና ቦታ ያላቸው ቪላዎች፤ መረን ለቆ ተንደላቆ የሚኖረው የገዢዎች፤ የጥቂቶች የባለጌ ኑሮ ኢትዮጵያ አደገች አያሰኝም። ሚሊዮኖች አሁንም ከቆሻሻ ክምር ስርና ዙሪያ ነው የሚኖሩት። ወያኔ ኢትዮጵያን ለዚህ ዳርጓታል–አረመኔ የሀገርና የሕዝብ ጠላት። ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ ኢትዮጵያና ጀግናው ሕዝቧ ለስቃይና ለሞት እንጂ ለሰላምና ለብልጽግና የታጩ አይሆኑም። እንኳን ለኢትዮጵያ ለመላ አፍሪካና ጥቁር ሕዝብ ሁሉ አርዓያ የሆነውን የአድዋ ድል በሚገባ ለማክበር የሚያማቸው ኢትዮጵያን የሚጠሉ ባንዳዎች መሆናቸውን  ሁሉም አውቋል። ለነገሩ የአክሱም ስልጣኔ እናንተን አይመለከትም ያሉን እኛ የተወለድነው ከወርቅ ሕዝብ ነው ብለው በይፋ ሰድበውንስ አልነበር?

ውሻ ካረጀ አዲስ ነገር መማር አይችልም እንደተባለው እነ ስብሓት ነጋና ሌሎቹ ጸረ አማራ ዘረኞች ወደ መቃብራቸው ሲያመሩ ሊሻሻሉና ከጸረ ሕዝብነት ሊርቁ አይችሉም። የሚመኙ ካሉ ራሳቸውን የሚያታልሉ–ምናልባትም አያ ከርስን ያስቀደሙ-ብቻ ናቸው።

ፍርድ ጎደለ ድሃ ተበደለ የሚል መንግስት በትግላችን እናምጣ የተባለው ከዚህ ውጪ መፍትሄ ስለሌለ ነው። ወያኔ በወንጀል እንደቀጠለ በዚህ የተነሳም ይወድማል። ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ተብሏልና፤ ትግል በወሬና በወረቀት ሳይሆን ባሩድ ከሚጤስበት ነውና ፤ ከሕዝብ ጎን ሆኖ መዋደቅና የህዝብንም ዕጣ መካፈል መቅደም አለበት። የሕዝብን ትግል መነገጃ ወይም ዝና ማግኛ አድርጎ ለመጠቀም መነሳትም የሚወገዝ ነው። ሀይል የህዝብ ነውና ለሕዝብ መቆም የሚፈልጉ ሁሉ ትሁትና የህዝብ አገልጋይ ሆነው መገኘትና በትግሉ ሜዳም መሰማራት አለባቸው። ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም ተብሏልና ከወሬው ቀነስ ከተጨባጩ ትግል ጨመር ማድረግ ወቅታዊ ግዴታችን ነው። አለበለዚያ ወያኔ ያዋርደናል፤ ይፈጀናል፤ ኢትዮጵያንም ውሎ አድሮ ያጠፋል።pdf_print

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገር አድን ትግል!!
ውድቀት ለወያኔ መንጋ!!