የጋራ ጠላታችንን በጋራ እንታገል!!

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ:  ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው ስፍራ፣ ባብዛኛው ቁጥራችን ለአገራዊ ጉዳዮቻችን ትኩረት ሰጥቶ አፋጣኝ መፍትሔ መሻቱ ላይ የወያኔ አፍዝ አደንግዝ ነግሶብን ቆይቷል። ስለአገራችን ሉዓላዊነት ፣ ስለሕልውናችን፣ ስለወደፊት ዕጣ ፋንታችን ወዘተርፈ ከግለሰቦችም ከቡድኖችም ቢነገረንም ዕዝነሕሊናችን ያደመጠ አልመሰለም።ከዚህ አንፃር አገር እንደአገር ፣ ሕዝብም እንደሕዝብ፣ እንዳይቀጥል የሚጎነጎነው ሴራ ቀጥሏል። ከመሐላችን የበቀሉ አሜኬላዎች እኛን መስለው ተደራጅተው ፣ በቡድን ተቧድነው ግን ከአገርና ከሕዝብ በተቃራኒ ቆመው ሊያጠፉን፣ ሊይስጠፉን ወደ ጠርዝ እየገፉን ይገኛሉ።  ሙሉውን ያንብቡ …