የጤና መድህን ክፍያ ታግዷል ትርኢት ቆይቶ የሚጫን ዕዳ ነው

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ:  ባለፉት 25 ዓመታት የተከሰተው የአፈና፣ የግጭት፣ የድሕናት፣ የውርደት፣ የዘረፋ፣ የሙስና —- ወዘተ ስርአት አውዳሚነቱ እንኳንስ ቀዳሚ ተጠቂ የሆኑት መምህራን በወያኔ የሐሰትና የተንኮል ፕሮፓጋንዳ ከጭቆና እንደወጡ ቆጥረው ጮቤ የረገጡ ግለሰቦችና ቡድኖችም ሳይቀሩ ደባውን ስለተረዱት ለመጸጸት ተገደዋል።  የወያኔ አገዛዝ ሲፋጅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ እንዲሉ የሕዝብ ቁጣ በሚያይልበትና በሚጋጋልበት ወቅት ሁኔታውን ለማቀዝቀዝና ራሱን ለማጠናከር የሚሠራውን ድራማ አያጣም።  ለዚህ አንዱ ማስረጃ በ2002ዓ.ም በአረብ አገሮች በግብፅና በቱኒዚያ ከተነሱት የሕዝብ አመጾች ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የህዝብ አመጽ ኣንዳይነሳ አቅጣጫ ለማስቀየር በጥድፊያ የተቋቋመው የአባይ ግድብና የተፈጸመው የአገርና የህዝብ ንብረት ዝርፊያ አንዱ ነው።  ሙሉውን ያንብቡ …