የፖለቲካ አክሮባት፣ አቅጣጫን ለማሳት፤ የፕሮፓጋንዳ ግብዐት፣ ውሸትን ለመንዛት

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ:  ባለፈው ሳምንት፤ እንደልማዳቸው፤ የሻዐቢያና የወያኔ አበጋዞች፤ የፕሮፓጋንዳ ኩዴታ አካሂደው ጊዚያዊ ውዥንበር ለመፍጠር ሞክረው ነበር።  ሊወናበድ የሚፈልገው ሁሉ ስለተወናበደላቸው፤ ምናልባት፤ ጊዚያዊ ስኬት እንዳገኙ ቆጥረውታል።  ሆኖም፤ ከሰሞነኛ ወሬ ሊያልፍ የሚችል እርባና ግን አላመጣላቸውም።  የሁለት ወንድማማች ዜጎችን አብሮነትን በማፋለስ የአካባቢ ሠላምና መረጋጋት እንዳይኖር ማድረግ፤ ከሕዝብ የሚመጣባቸውን አደጋ ለመከላከል ይረዳናል ብለው አስበው ከሆነ፤ ያም፤ አልተሳካላቸውም።  ዜጎችን እያጋጩና እያለያዩ መቀጠል ለሥልጣናቸው ማራዘሚያ ዘዴ ሊጠቀሙበት መከጀላቸው እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አልነበረም።  ሻዕቢያዎቹ 200 የወያኔ ወታደሮች ገድለን፤ ከሦስት መቶ በላይ ወታደሮችንም አቁስለናል ብለው ቢለፍፉም፤ ወያኔዎቹ ግን “በቆረጣ ውጊያ የሚችለን የለም!” ከሚሉት የጉራ ደንፋታ ያለፈ መግለጫ ሲሰጡ አልተደመጡም።  ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ …