ይድረስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች በያላችሁበት

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ – ትውልድ እያለፈ ትውልድ ይተካል። ዘመንም በዘመን እየተተካ ያልፋል። ትውልድና ዘመን መፈራረቃቸውና መተካካታቸው የተፈጥሮ ህግ በመሆኑ ፤ ትውልድ በትውልድ፤ ዘመንም በዘመን እንዳይተካኩ ሊያድርግ የሚችል አይኖርም።  ቢኖርም አይስካለትም።  የቆየው ትውልድ ለሚተካው አዲስ ትውልድ የሚያስተላልፈው ቅርስ ያማረ፤ የተዋበ፤ ወይም የከፋ የከረፋ፤ አኩሪ ወይም አሳፋሪ፤ ሊሆን ይችላል።  ተረካቢው ትውልድ ሊያስረክብ የሚችለው፤ የተረከበውን ብቻ ሳይሆን፤ ያልተረከበውንም ጭምር ነው። ያልተረከበውን-ያልዋረሰውን ሲባል በራሱ ዘመን የሆነውን፤ የተደረገውን የተፈፀመውን ብቻ ለማለት ነው።  ባልተረከበው ላይ ተጠያቂ አይደለም።  ያለፈውን ዕዳ ከፋይ እንዲሆን አይጠበቅበትም።  ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ