ደብዛቸው ለጠፉ ታጋዮች በዊንፔግ፣ ካናዳ ሕዝባዊ ምሽት

በሰውነት ፈቃዱ፡ እስካሁን ብቻ ከ$280 ሚሊዮን ብር ወጭ ሆኖ የተመሰረው የካናዳ ሰብአዊ መብት ሙዚዬም ለሕዝብ ክፍት ከተደረገ በኋላ በዊንፔግ፣ ካናዳ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ከሌሎች በአካባቢው ከሚገኙ ለሰው ልጅ መብት መከበር፣ እኩልነትና ነፃነት ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት በዓለም ውስጥ ከተለያዩ አገሮች ለሰው እኩልነት፣ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር፣ ለፍትሕና ለነፃነት ሲታገሉ ድብዛቸው የጠፉ ታጋዮችን የሚያስታውስና ለወደፊቱ እንደዚህ ዓይነት ድርጊት እንዳይፈጸም ምን መደረግ እንዳለበት የሚያሳስብ ሕዝባዊ ምሽት ቅዳሜ፣ ጥቅምት 15 ቀን 2007 ዓ.ም (Saturday, October 25, 2014) የካናዳ ኢሚግሬሽን ሚኒስቴር፣ የዊንፔግ ከተማ ገዢ ለመሆን ውድድር ላይ የሚገኙት ግለሰብ፣ በዊንፔግ ከተማ የሚገኛው ቅድስተ ማርያም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አስተዳደሪ አባት አባ ፍቅረስላሴ፣ ከተለያዩ ድርጅቶች ተወካዮች፣ ከሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስራኞች አንድነት ኮሚቴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለት አባላት፣ ጋዜጣኞች፣ ከዊንፔግ አካባቢ የመጡ ኢትዮጵያዉያንና የሌላ አገር ዜጎች በተገኙበት በWest End Cultural Centre, Winnipeg, Manitoba, Canada ሕዝባዊ ምሽት ተደርጓል። ሙሉውን ዘገባ ያንብቡ …