ጉንዳን ሳይገባ አመድ ነስንስ

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ: በረዥም ዘመናት ታሪኳ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ጥቃት የደረሰባት፤ በአመዛኙ፤ ከባዕዳን ኃይሎች በበለጠ በሀገር ውስጥ ከሃዲያን ነበር ቢባል፤ ስህተት አይሆንም። የውጭ ወራሪ ኃይሎች ነፍጥ አንግበው ሲመጡባት፤ የውስጥ ባንዳዎች በበኩላቸው፤ ስጋጃ አንጥፈው ተቀብለዋቸዋል። ዋገምት ደግነው፤ ደሟን እየመጠጡ፤ ለበዕዳን ወራሪ ኃይሎች አስተላልፈውላቸዋል ። የሀገሪቱን ውስጠ ምሥጢር እያሾለኩ አቀብለዋቸዋል። የሚገርመው ደግሞ፤ ይህንን የክኅደት ተግባር የፈፀሙት ፤ በአብላጫው፤ ገበሬዎችና ተራ ዜጎች ሳይሆኑ፤ ሹማምንቱና በኃላፊነት ቦታ የተቀመጡ ሰዎች ነበሩ። … ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ