ግቡን ያልመታ ዓላማ፤ ሂደቱን ያላገባደደ ትግል

ሊነበብ የሚገባ ወቅታዊ ሐተታ ከፍኖተ ዴሞክራሲ ሬዲዮ፡ በመርኅ ፅናት፤ በራስ መተማመን፤ በሀገር ፍቅርና በሕዝብ ወገንተኝነት ላይ የተመሰረተ የነጻነት ትግል፤ ፈጠነም ዘገየ ግቡን መምታቱ አይቀሬ ነው። በዓላማ ፅናት ላይ የተመረኮዘ ትግል ድልን መጎናጸፉ አጠራጣሪ አይሆንም። ይህ ደግሞ አፍ እንዳመጣ የሚነገር ሳይሆን፤ በታሪክ ተበጥሮ የተመሰከረለት ሀቅ ነው። ለአለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት፤ በሀገራችን፤ ሁለት ተጻራሪ ኩነቶች አልተለወጡም ። አንደኛው የአምባገነን ሥርዓት፤ መልኩን እየለዋወጠ ተንሰራፍቶ መቀጠሉ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፤ ተዳፍኖ ያልተዳፈነው የሕዝብ አመጽ ነው። ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …