ግብጽ በአባይ ጉዳይ በወያኔ ላይ የበላይነትን መያዟ

(ከፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ)-  ግብጽ በአባይ ጉዳይ በወያኔ ላይ የበላይነትን መያዟ ታወቀ – ረሃቡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጉዳት እያስከተለ ነው – የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል መደረጉ አዋጁ የታለመለትን ግብ እንዳልመታ ያሳያል ተብሏል – የሰብዓዊ መብት ጥሰት መረን የለቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ገለጸ።

በአባይ ጉዳይ በተነሳ ግብጽ በአባይ ተፋሰስ ሀገሮች ተንቀሣቅሳ በወያኔ ላይ የበላይነትን መያዟ ታወቀ። ወያኔ እያንቀላፋ ባለበት ሁኔታ ግብጽ የተፋሰሱን ሀገሮች በተለይም ዩጋንዳን፣ ደቡብ ሱዳንን፣ ሱዳንን በመገናኘትና በማሰባሰብ ቀደም በኤንተቤ ዩጋንዳ ተደርጎ የንበረውን ስምምነት ለማፍረስ እየተቃረበች ነውም ተብሏል። የኤንቴቤው ስምምነት ግብጽ በእንግሊዝ ቅኝ ገዚዎች የተሰጣትን የውሃ ድርሻ ሰርዞ የተፋሰሱ ሀገሮች ያላቸውን መብት ያረገጋጠ ነበር። ግብጽ ማንኛውም ሀገር በአባይ ላይ ግድብ ሊሰራ ሲያቅድ፤ በቅድሚያ ግብጽን ማስፈቀድ አለበት፤ ሁሉም ውሳኔ በሁሉም ተፋሰስ ሀገሮች ስምምነት መደረግ አለበት የሚለውን ማስረገጥ የምትፈልግ ሲሆንበዚህ መስክ ዩጋንዳና ደቡብ ሱዳንንን ማግባባቷ ታውቋል። ወያኔ እስራዋለሁ ያለውን ግድብ በገንዘብ እጥረትም ሆነ ራሱ ጥቅም ለማግኘት እያደናቀፈው ያለ ቢሆንም ይህ የጉራ ስምሪቱ ፈቅ እያለ አለመሆኑን የተቹ ውስጠ አዋቂዎች በአባይ ንትርክ ግብጽ የበለይነትን ይዛ መገኘቷን ከቶምመካድ አይቻልም ብለዋል።

ባዕድ ሀገሮች ማለትም አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ የገባውን የረሃብ አደጋ በተመለከተ ኢትዮጵያንና ኤርትራን ባይጠቅሱም ረሃቡ ሁለቱንም በሰፊው እያጠቃ መሆኑንና ይህ በጊዜ ተጋልጦ ለተጠቂዎቹ አስቸኳይ እርዳታ እንዲደርስ ያስፈልጋል ሲሉ ያካባቢውን ሁኔታ የሚከታተሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች አሳስበዋል። በአፋር አካባቢ፣ በኦጋዴን፣ ሰሜን ሸዋ … ወዘተ የረሃቡ ሁኔታ ተስፋፍቶ አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ነው ያሉ ክፍሎች፤ ባዕዳን ይህን ማንሳት የተሳናቸው የሚደግፉትና ዕድገት አመጣ የሚሉት ወያኔ እንዳይጋልጠባቸው ነው በሚል ጠቁመዋል።

የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ ሺዎች ቢገደሉና ቢታሰሩም ይህን ለወያኔ መውጫ መተንፈሻ አልሰጠውም ብለው የደመደሙ ታዛቢዎች አዋጁ ከስድስት ወር በላይ እንዲቀጥሉ መደረጉ ይህን ያረጋግጣል ብለውም ተችተዋል። የብረት ትግሉ በጎንደር መስፋፋቱ መቀጠሉ በአንድ በኩል ሲታይ አመጹ ግን በየፈርጁ እየሰፋ መገኘቱን በመካሄድ ላይ ያለውን የመምሕራን አድማ በመጥቀስ ተቃውሞው እየሰፋና ሀገራዊ ይዘቱም እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀና ኮማንድ ፖስት የሚባል የወያኔ ተግባራዊ ተቋም ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መረን እንደለቀቀና ወደ 50 ሺ የሚጠጉ ዜጎች ከመታገታቸው ባሻገር ብዙዎቹ ግብረ ስየል እንደተፈጸመባቸው ገልጾ የወያኔን አገዛዝ አውግዟል። በአዋሽ በረሃና መሰል ቦታዎች የታገቱ ዜጎች አሁንም በመሰቃየት ላይ መሆናቸውንና ታስረው የተፈቱም የመጨረሻ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደተለቀቁ ጠቁመዋል። ጋዜጠኞች፣ ምሁሮች፣ አባቶቻቸው በወያኔ የተገደሉ፣ በኢሕአፓነት የተጠረጠሩ፣ አክራሪ አማራና ኦሮሞ የተባሉ ሺዎች ታግተውና በመሰቅየት ላይ እንዳሉም ኮሚቴው ገልጧል። ይህን በሚገባ አጋልጦ በማውገዝ ፈንታ የሚደባብቁትን ኮሚቴው በጥብቅ የሚያወግዝ መሆኑንም ገልጧል።

ዝርዝር ዜናዎችና ኃተታ ከፍኖተ ያዳምጡ።