ጓድ ኢብራሂም አብዱልቃድር (ብርሃን)

ጓድ ኢብራሂም አብዱል ቃድር (የትግል ስሙ ጓድ ብርሃን) የተወለደው በጎንደር ክፍለ ሀገር አዳርቃይ ከተማ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው ኢሕአፓን በመቀላቀል በተለያዩ ቦታዎች ታግሏል። በ 1976 ዓ.ም ወደ ሱዳን አገር ከገባ በኋላ በድርጅቱ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ተመድቦ አገልግሏል። መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በድንገተኛ ሁኔታ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ጓዱ የአገርና የወገን ፍቅር ያልተለየው፥ በአመነበት ጸንቶ የቆየ ቆራጥ ታጋይ ነበር። እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በኢሕአፓ አባልነቱ ሲታገል ቆይቷል። ጓድ ኢብራሂም አብዱልቃድር የእንዲት ሴት ልጅ እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።  ክብር ለሰማዕታት።