ጸጋዬማ ጸጋችን ነው!

ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል: እነ ፀጋዬ ደብተራው ለዘለዓለም ሕያው ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት ናቸው፡

አሲምባ ድረ-ገጽ: የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድርጅቶች ጉዳዩ ቢቀርብላቸውም ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸውና በተለየ ደግሞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት እንታገላለን የሚሉን ወገኖች እነፕሮፌሰር መስፍን መሠረቱት የሚባለው ኢሰመጉ ሳይቀር የነፀጋዬ ደብተራውን ጉዳይ ሲሸሹ፣ ሲሻቸው ምንም ዕውቅና ላለመስጠት የተመከሩ ይመስል ምክንያት ሲደረድሩ፤ ገሚሶቹ ደግሞ በሚያሳዝን ሁናቴ ድርጅቱ ይጠይቅላቸው ሲሉም ይደመጡ እንደነበር ይታወቃል።  ሌላው ቀርቶ ገና ከጧቱ ወያኔ ሥር ሳይሰድ እነፕሮፌሰር አሥራት ሲታሰሩ በቁጣ ተሰልፈው የወጡ ኢትዮጵያውያን መካከል በድጋፍ የወጡ የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች የነፀጋዬ ደብተራውን ስምና ምስል ይዘው በሰልፉ በመሳተፋቸው በሌላው ወገን ይደርስባቸው የነበረውን ግልምጫ ማስታወሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።  ሙሉውን ጽሑፍ ያንብቡ …

(አንሙት ከለንደን)

 

ጸጋዬማ ጸጋችን ነው!
አብሮን ያለ፣ እኛም ያለነው፣
ጸጋዬማ ጸጋችን ነው፣

በመኖራችን የሚኖር፣
ስታፍኑት የሚናገር፣
ስታሥሩት ፈቶ ‘ሚበር፣
ስታጨልሙት የሚያበራ፣
በብሩህ መንገድ የሚመራ፣
ፋኖ መሪ፣ የጀግና አውራ፣
ለሞቱ ድግስ የሚያቅራራ፣
የትውልድ ፈርጥ፣ ‘ሚያኮራ!
ሙሉውን ግጥም ያንብቡ …