ፋኖ ማርሺ ቀይር እና ሌሎች ግጥሞች

በዓይነኩሉ ባላገር

የኢትዮጵያ ፋኖ ፎክሮ ተቆጣ ፤
የሀገሩን ጠላት ጠንቅቆ ሊቀጣ ፤
የሆዳም አስክሬን እንደ ጉድ ሊሰጣ ፤
ማምለጫ የሌለው መራራ ቀን መጣ ፤
ወንድነት የሚለይ ጠቋራ ቆምጣጣ ፤
የኖረውን ስቃይ ከሀገር ሊያስወጣ ፤
ባንዳን ከነዘሩ መንጥሮ ሊቀጣ ።

አሁን ጊዜው አልቋል አስራ አንድ ሰዓቱ፤
የሀገሬ መሪ ይታወጅ መንግሥቱ ፤
የአራት ኪሎ ገዳይ ጋቢናው የቀረው ፤
ጎማ እና ካሶኒው ተቃጥሎ ያለቀው ፤
በለኮሰው እሳት ተቃጥሎ ሊሞት ነው፤
አምሳያው ወንድሙ ሸኔም አላዳነው ፤
የወያኔም ጩኸት ከጉድ አላስቀረው ፤
ተምሷል በአንድ ላይ ሁሉም ጉድጓዳቸው ፤
ኢትዮጵያ እፎይ ልትል ሴት ወንዱ ሊያርፋቸው ።

ፋኖ ማርሽ ቀይር ብረር እንደ አሞራ ፤
ቤተ መንግስት ገብተህ የድል ፋናን አብራ ፤
ህዝብ የሚወደውን ሀገረ መንግስት ስራ ።