ውበት ያለው ግን የተመጠነ


ደብዳቤ ከደሊላ ዱኪ ዘገዬ

ውድ ደብተራዎች!

ይህንን ዓላማ ወደውና ፈቅደው ውድ ህይወታቸውን ከሰጡት የዚያ ጊዜ የዘመኑ ፈርጦች ውስጥ አንዱ አባቴ ስለሆነም አባቴም ተሰልፎ ስለተሰዋበት ገድል የሚያወራውና የሚተርከው “ዝብርቅርቅ ማህደርን” ሳዳምጥ፣ ደስታ አየሉት ሃዘን ሁለት ስሜት ተሰምቶኛል። ስለ እውነት ልናገርና አባቴ ስለተገደለበት ሁኔታ እኔ ልጁ ለአቅመ አዳም እስክደርስ ድረስ እየተነገረኝ ያደኩት፣ በሹክሹክታ፣ በፍርሃት፣ በሰለለ ድምፅና አንደበት ነው። ደብተራዎች በ እንደዚህ ዓይነት ሰቀቀን ውስጥ የሚኖሩ እናቶችና እኛን መሰል ልጆች ደግሞ ብሁሃን ለመሆናችን ስገልጥላችሁ አሁንም መሪር ሃዘን ይሰማኛል።  ሙሉውን ደብዳቤ ያንብቡ.....