የተነጣጠለ ሕዝባዊ አመፅ፤ ያልተቀነባበረ ሀገራዊ ትግል ግቡን አይመታም !

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሬዲዮ ሀተታ (ጥር 13 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ):  ለዘመናት ሲከማች የቆየው የሀገራችን ችግር፤ መፍትሄው አሁንም እንደ ምድረበዳ ንብልብሊት ( ሚራዥ) የማይጨበጥ እየሆነ መሄዱን ቀጥሏል።  ተከሰተ ሲባል፤ ይሰወራል።  ተጨበጠ ሲባል ያፈተልካል።  ተከታትለው ቢይዙትም ያመልጣል። የሀገራችን ችግርና መፍተሄው ሊገጣጠሙ አልቻሉም። ሰኔና ሰኞ አላገጣጠማቸውም።  መፍትሄውን ፍለጋ የተሰማራውም ሁሉ፤ ጥረቱና ድካሙ ያተኮረው፤ በመፍትሄው ፍለጋ ላይ ሳይሆን፤ ገና በችግሩ መኖር አለመኖር ላይ የሚዋትት ይመስላል። የችግሩን ጥልቀትና ስፋት መረዳቱ ሳይሆን፤ እንዲያው ከነአካቴው ችግር መኖሩንም የተገነዘበው አይመስልም።  የሀገሪቱን ችግር ካለተረዱ ደግሞ፤ መፈትሄ ፍለጋ መሄድ አይቻልም። ወይም ደግሞ፤ ” ስለችግር መስማት ሰልችቶናልና እባካችሁ አታስቸግሩን፤ ኢትዮጵያ እንደሆነች፤ ዝንተ-ዓለሟን ከችግር የምትወጣ ሀገር አይደለችም ” ካልተባለ በስተቀር!  ሙሉውን ሐተታ ያንብቡ…