ለዓባይ መቀራመት ፤ ኢትዮጵያን ማጥፋት: የሱዳንና የግብፅ መሪዎች ፤ በካርቱም ከወያኔ ጋር የተፈራረሙት ውል ኢትዮጵያን የሚጎዳ ሰነድ ነው

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ (መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ): በመጋቢት 14 ቀን 2007 ዓም ( ማርች 23 2015) በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ላይ፤ የግብጽና የሱዳን መሪዎች ተገናኝተው በዐባይ ወንዝ ኣጠቃቀም ዙሪያ ከወያኔ ወኪሎች ጋር አንድ ስምምነት እንደተፈራረሙ ተገልጿል።   የስምምነቱንም ሰነድ ይፋ አድርገዋል። ግብጾችና ሱዳኖች ለየሀገሮቻቸው የሚጠቅም ውል ተፈራርመው መሄዳቸው የሚያስገርም አልነበረም።   የዚህን ስምምነት ወሬ የሰሙ የተለያዩ የዜና አውታሮች በሰፊው አስተጋብተውታል። ቢቢሲና ኢ.ኤፍ. ፒ. ሰፊ ሽፋን ሰጥተውት ነበር።   ኢየሩሳሌም ፖስት የተሰኘው የእስራዔል ዕለታዊ ጋዜጣ እንደ ሰበር/ትኩስ/- ዜና ደርጃ አቅርቦ፤ በሰፊው አትቶበታል።   አል አህራም የተሰኘው የግብፅ ዕለታዊ ዐረብኛ ጋዜጣም በበኩሉ ሰነዱን በተለያዩ ቋንቋዎች ትርጉሞ አሳትሞ አሰራጭቶታል።   አል አህራም ጋዜጣ በሰነዱ ላይ ላሜ ወለደች ብሏል። ሁሉም ይህንን ማድረጋቸው ፤ የየራሳቸው ምክንያቶች ስለአሏቸው ነው።  ሙሉውን ያንብቡ