የሴቶች ተሳትፎ ለትግሉ ወሳኝ ነው

ዴሞክራሲያ (ቅጽ.41 ቁጥር 6 መጋቢት 2008 ዓ.ም): የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት የታገለላችውና ክቡር ህይወቱን የገበረላችው መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች ዛሬም ምላሽ አላገኙም። ወያኔና ባዕዳኑ በኢትዮጵያ ሰላም ሰፈነ፤ የኤኮኖሚ እድገት ተመዘገበ፤ ማሀበራዊ ጭቆናዎች ተወገዱ በማለት ቢሳለቁም፤ ሕዝቡ ሰብዕናውንና ክብሩን ፤ የዜግነት መብቱን ለማስጠበቅና ዕውን እንዲሆኑ ለማድረግ በሚችለው መንገድ ሁሉ አምባገነኖችን ከመታገል አላቆመም። ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሮ ተራማጅ ምሁራን በተለይም በኢሕአፓ ዙሪያ የተሰባሰቡትና መሠረታዊ ለውጥን ያቀነቀኑት ወጣቶች ካነሷቸው ዓቢይ መፈክሮች ውስጥ አንዱና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥያቄ አካል የሆነው የሴቶች የፆታና የእኩልነት ጥያቄ ዛሬም ምላሽ ሳያገኝ ወቅታዊነቱን እንደተላበሰ ይገኛል። ሙሉውን ያንብቡ . . .