የት ደርሰናል? ምንስ አትርፈን ምንስ ማሻሻል አለብን፣ ለወደፊት?

ዴሞክራሲያ ቅጽ.41 ቁጥር 8 (ግንቦት-ሰኔ 2008 ዓ.ም):  ማናቸውም ዓላማና ግብ ያለው እንቅስቃሴ በሂደቱ የተጓዘበትን ጎዳና በአንድ በተወሰነ ወቅት ላይ ጊዜ ወስዶ ወደ ኋላ መለስ ብሎ መቃኘት ይኖርበታል። በዚህም የደረሰበትን፥ አብሮም እዚያ ለመድረስ ባረገው ጉዞው የወጣ የወረደበትን፣ ያጣውን ያገኘውን፣ ያጠፋውን ያለማውን፣ ጥንካሬውን ድክመቱን፣ የሚያስተውልበት ብቻ ሳይሆን ለእንግዲሁ የዓላማውን ግብ መሳካት ሊያፋጥኑ ይችላሉ የተባሉትን አስፈላጊና ወሳኝ ዝግጅቶችን ለመንደፍና ለማቀድ፤ ብሎም ለተፈፃሚነታቸው መወሰድ ያለባቸውን ማናቸውንም እርምጃዎች ለማቀናጀት እንዲያስችለውም ጭምር ነው። ይህ የስርዓት ለውጥ ኣንዲመጣ ለሚታገል ህዝባዊ እንቅስቃሴ ደግሞ አስፈላጊና የግድ መሆን ያለበት ብቻ ሳይሆን ወሳኝነትም ያለው ጉዳይ ነው።  ሙሉውን  ያንብቡ . . .