የወያኔን ጸረ ሕዝብ ግድያ በጥብቅ እናውግዝ፤ ትግሉም ይቀጥል!

ኢሕአፓ:  ትላንት እሁድ የባሕር ዳር ሕዝብ ያደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመበተንና በአጠቃላይም የተቀጣጠለውን የሕዝብ አመጽ እሳት ለማዳፈን ወያኔ በወሰደው የአፈና እርምጃ 30 eprp logoንጹህ ዜጎች ሲገደሉ ወደ 50 ቆስለው 60 ያህሉ ደግሞ ታግተዋል። ይህ ወንጀል በጎንደር ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ባለው ግድያና በሌሎች ቦታዎችም በተፈጸመው አፈና ላይ የተጨመረ ነው። አረመኔው ወያኔ ሰባት ሰዎች ሽብር ሊፈጽሙ ሲሉ ተገደሉ ብሎ ወንጀሉን ሊያቀልል መሞከሩም ተዘግቧል። ከዚህ በተጨማሪ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ አዲስ አበባን ጨምሮ በምዕራብ በደቡብና በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከ200 በላይ በሆኑ ከተሞች በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ የወያኔ ጦር በወሰደው እርምጃ ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውና በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ተዘግቧል።  ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ