ፉክክር: ብሔርተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ

ዩሱፍ ያሲን:  በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ቀጣይነት ሊኖረው የሚችል ሁኔታ አይደለም (Unsustainable) ሲባል ሰንበትበት ብሏል። አንድ ሓሙስ ቀረው እየተባለ መነገር የጀመረው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። የሥርዓቱ እድሜ ካንድ ሓሙስ ይልቅ ከላይ ወደ ዜሮ በሚደረግ የኋሊት መቁጠር የሚዳዳቸው ታዛቢዎቹም አሉ። በፈረንጅኛው Count Down  የሚሉት ስሌት መሆኑ ነው። እንደ ተለመደው ኢትዮጵያ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ ቆማለች፣ በመንታ መንገድ ላይ ናት መባሉ እንደገና እየተዘወተረ መጥቷል። ሁሉም ግን ኢትዮጵያ ወዴት? የሚለውን ጥያቄ እያስጨነቀው ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ መቆሟ አያነጋግርም። ወያኔ/ኢሕአዴግ አንድ ሓሙስ ቀርቷታል ትንበያ ላይ ሁላችን ባንስማማም በለውጥ ዋዜማ ላይ ናት መባሉ ያስኬዳል። “በለውጥ ማዕበል ዋዜማ ላይ መገኘቷ ሁሉን ቢያስማማም የጉዞዋ አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ግን አነጋጋሪ ይሆናል። አገራችን በዲሞክራሲ ለውጥ አቅጣጫ ትከንፋለች ወይስ ፍርስርሷ ወጥቶ ትበታተናለች? ምኞትና ሟርት፣ ተስፋና ስጋት የሚደበላለቅ ቢሆንም መፃኢ እጣ ፋንታዋ ብዙዎችን ስጋት ላይ ጥሏል። የተወሰኑ ዜጎቿን ያስቆዝማል፤ ያሳስባልም።  ሙሉውን ጽሁፍ ያንብቡ . . .