የሽግግር ወቅት

ዴሞክራሲያ የኢሕአፓ ልሳን (ቅጽ 42፣ ቁ. 2፣ ጥቅምት/ ኅዳር 2009) – በማንኛውም የሥርዓተ ማኅበር ልውውጥና ሂደት የሚተላለፍ ኅብረተሰብ፣ ተወደደም ተጠላ፤ የሽግግር ወቅት የሚያስፈልገው መሆኑ አያከራክርም። ለዚህም በቂ ምክንያቶች ይኖራሉ። በቅርቡ የሀገራችን ታሪክ እንኳን ሦስት ተፃራሪ ሥርዓቶች፣ ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት ሲለዋወጡ የተመለከትን ሲሆን በሥርዓቶቹ ልውውጥ መካከል ለተተኪው ሥርዓት መተላለፊያ፤ ማስተናገጃና መቆጣጠሪያ ሊሆኑ የሚገባቸው በቂ ዝግጅቶችና መሰናዶዎች ሳይደረጉ ቀርተዋል። ሂያጁውን ማስወገድ እንጅ፤ መጭው ምን እንደሚመስል እንኳን በቅጡ ሳይታወቅ በመታለፉ፤ በሁሉም መስክ አገራችን መጎዳቷን ሁሉም ዜጋ የሚያውቀው ዕውነታ ነው። የዚህ ውጤትም የማያቋርጥ ፀፀትና ቁጭት ሆኖ ቀርቷል። “አርቆ ማሰብ አቅቶኝ፤ በግብታዊነት እጄን በእጄ ቆረጥኩት” የሚያሰኝ ትካዜን ጥሎ ሄዷል።  ሙሉውን እትም ያንብቡ…