የኢትዮጵያ ወጣቶች ቀጣይ ትግል ቀጣይ ቃል ኪዳን

(ዴሞክራሲያየኢሕአፓ ልሳን፣  ቅጽ 42፣ ቁ. 3፣ ታኅሣሥ 2009):  በወጣትነት እድሜያቸው ኢሕፓን የመሠረቱትም ሆነ በኋላም የድርጅቱ አባልና ደጋፊ በመሆን በትግሉ ውስጥ የተሳተፉት ወጣት ምሁራንና ተማሪዎች ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በኢትዮጵያዊነት የተሰባሰቡ፤ በአንድ ዓላማና ፍላጎት ( በአገር ፍቀር ሰሜት) የተሳሰሩ ለመሆናቸው፣ በጊዜው የከፈሉት መከራና ስቃይ ይመሰክራል። በትግሉ ሂደት ያለፉትም ሆነ እስከዛሬም ትግሉን በፅናት ያስቀጥሉ አባላትና ደጋፊዎች ገድልም ይህንኑ አስረግጦ ይናገራል። ይህ በአያሌ ኢትዮጵያውያን የህይወት መሰዋዕትነት የተከፈለበት የለውጥ እንቅሰቃሴ ምላሽ ባላማግኘቱ ዛሬም የሕዝብን ትግል ማስፋፋትና ማጠናከር ግድ ሆኖ ይገኛል። በየወቅቱ የነበሩትን የአምባገነንና የፈላጭ ቆራጭ የአገዛዝ ሥርዓትን በማስወገድ፣ በምትኩ ፍትህ እኩልነትና ዴሞክራሲ እውን የሚሆንበት ሥርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ የተደረገው የትግል ጉዞ እጅግ አስቸጋሪ ወጣገባና ውስብስብ ነው። ከበርካታ ዓመታት በላይ የፈጀውና አሁንም ቢሆን ለውጥን አርግዞ በጉዞ ያለው ሕዝባዊ ትግል ያሳለፈውን ውጣ ውረድ እንዲሁም በትግሉ ውስጥ የተከፈለውንና ዛሬም ጭምር እየተከፈለ ያለውን መስዋዕትነት በአንክሮ ማሰብና ትልቅ ክብርም መስጠት ይገባል። ሙሉውን እትም ያንብቡ