ውይይትና ድርድር ለምን ዓላማ?

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ:  ……. የሰሞኑ፤ ከወያኔ ጋር የዕርቅና ሠላም ውይይትን አስመልክቶ በየቦታው የተለያዩ ውዥንብሮች፤ ውቂው- ደብልቂውና ትርኪ-ምርኪዎች፤ ከአንዳንድ አካባቢዎች ይሰማሉ።  በወያኔ በኩል የሚነፍሰው ይኽ አቅጣጫ አስለዋጭና ትጥቅ አስፈች ፕሮፓጋንዳ፤ ያገዛዙን ጊዜ ለተወሰኑም ቀናት ቢሆን ለማሰረዘሚያ ከሚደረግ ጥረት አያልፍም። ወያኔ ይኽንን ቢያደርግ አያስደንቅም። ለአርሱ፤ የሞት-ሽረት ጉዳይ ነውና! በሥልጣን ቆይቶ መዘርፍ ወይም ከሥልጣን ተባርሮ ቀልጦ መቅረት ነው። ወያኔ ደግሞ ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢል፤ በሠላም ሆነ በፈቃዱ ከሥልጣኑ የሚወርድ ቡድን አይደለም። ከየትስ የተማረው?  ሙሉውን ሀተታ ያንብቡ