የኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር አካል በኖርዌይ ያደረጉት የሥራ ጉብኝትና ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት ተጠናቀቀ

በመጀመሪያ ከኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የምሥራቅና የምዕራብ አፍሪካ አገራት ኃላፊዎች፣ ከላንድኢንፎ፣ ከኖርዌይ ኢሚግሬሽን ዳይሬክቶሬት የኢትዮጵያ ክፍል ኃላፊ፣ የስደተኞችን ጉዳይ ከሚያየው ክፍልና ከኖርዌይ የስደተኞችን መብት ከሚያስከብረው ተቋም ጋር ሰፊ ውይይቶችን በተለያዩ ቀናት አካሂደዋል። በነዚሁም ውይይቶች ባለው ተጨባጭ ሁኔታና ኢሕአፓ እያደረገ ባለው ትገል ዙሪያና በውያኔ የግፍ አገዛዝ ምክንያት ለስደት እየተዳረጉ በኖርዌይ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና የድርጅታችን አባላት የስደተኞች መብት መከበር ጉዳይ በስፋትና በጥልቀት ተወያይተዋል።

የካቲት 11 ቀን 2009 ዓም ኢሕአፓ ኖርዌይ ክፍል የህዝብን የተለያዩ ብዥታዎች እና ወቅታዊ የሃገራችንን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ህዝባዊ ውይይት ማድረጉ ብዙ ያስተምራል ብሎ በማመን ለዚህም ይመጥናሉ ያላቸውን እንግዶች በመጋበዝ እድምተኞችን የማረከ ለነበራቸው ጥያቄዎች መልስ የሚሆን ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ሆኖ እንደታሰበውም አስተማሪ ሆኖ አልፏል። ከተጋበዙት እንግዶች መካከል ከኢሕአፓ ከፍተኛ አመራር አቶ እያሱ አለማየሁ በሃገራችን ወቅታዊ ሂደት ላይ፤ አሁን ባለው የህዝብ ትግል ላይ፤ የወያኔን የመከፋፈል ሴራ፤ የህብረትን በጎነት አሁን ላይ ያለን እንቅፋት ሌሎችንም አንስተው ህዝብን በሚማርክ በሚቀሰቅስና በሚያስተምር ሁኔታ ሃሳባቸውን አብራርተዋል።

ጸሃፊው እና የምስራቅ አፍሪካ ኤክስፐርት የሆኑ አቶ ዩሱፍ ያሲን እና ወጣቱ ዶ/ር ተክሉ አባተ የማንነት ፖለቲካ፤ ብሄርተኝነት፤ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እና የአማራው ፖለቲካዊ ንቅናቄ እና አንድምታው በሚል ርእስ ላይ ከወትሮው ለየት ባለና ጠለቅ ያለ ይዘት ያለው ትንታኔ አቅርበዋል። ሙሉውን ዘገባ ያንብቡ….