በላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤቶች ፈረሱ

ሂውማን ራይትስ ዎች በዶክተር መረራ ላይ የቀረበው ክስ ፖለቲካ መነሾ ያለው የበቀል እርምጃ ነው አለ – በአዲስ አበባ በላፍቶ ክፍለ ከተማ የፈረሱት ቤቶች ውዝግብ አስከትለዋል – የአባይ ግድብ የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅሙ ከ6000 ወደ 6400 አድጓል መባሉ ግብጽን ያሳሰበ መሆኑ ተነገረ።

ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ሰኞ የካቲት 20 ቀን 2009 ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀ መንበር በሆኑት በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የቀረበው ክስ ለፖለቲካ ተቃውሞ የተደረገ የበቀል እርምጃ ነው በማለት የወያኔን አገዛዝ አወግዟል። የሰብአዊ መብት ተቋሙ በዚሁ መግለጫው ዶ/መረራ በአገር ውስጥ በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመው የፖለቲካ ድርጅት መሪ መሆናቸውን ገልጾ የታሰሩትም ለአውሮፓው ማህበር ስለአገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ገለጻና ማብራሪያ አድርገው ሲመለሱ መሆኑን ዘርዝሯል። የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ አላቸው በማለት ብቻ በፈጠራ ክስ ወንጅሎ ለመቅጣት መሞከር ፖለቲካዊ መነሾ ያለው ከመሆኑናና ከበቀልተኛነት አያልፍም ብሏል። በአገሪቱ ውስጥ በነጻና በግልጽ ተወያይቶ እውነተኛ ሰላም ማስገኘት የሚቻለው ዶ/መረራ ጉዲና፤ ዶ/በቀለ ገርባና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ሲፈቱ መሆኑን ገልጾ ሁሉም ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪውን አስተላለፏል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 300 ቤቶች እንዲፈርሱ ማድረጉ ብዙ ውዝግብ ማስከተሉ ታውቋል። እንዲፈርሱ የተደረጉት ቤቶች በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል በሚባለው ወሰን ላይ ያሉ በመሆናቸውና መሬትን በመቀማት ከተማዋን ማስፋፋት የሚለውን አመለካክት በማስረጹ ሕዝባዊ ተቃውሞ ይቀሰስቅሳል የሚል ስጋት ፈጥሯል ተብሏል። በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባው አስተዳደር ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ በበተለያዩ የከተማዋ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ እቅድ ያለው መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ ከሚያውቁ ዜጎች ለማወቅ ተችሏል።

ከጠቅላላው ስራ ገና አምሳ ከመቶ ብቻ ተጠናቋል የሚባለው የአባይ ግድብ የኃይል ማመንጨት አቅሙ ከ6000 ሜጋዋት ወደ 6400 ሜጋዋት ከፍ ብሏል መባሉ የግብጽና የሱዳን ባለስልጣኖችን ያሳሰበ መሆኑን ኢጅፕት ኢንዲፔንደንት የተባለው ጋዜጣ በአምዱ ላይ አስፍሮ አውጥቷል። ከሶስቱ ወገኖች የተውጣጡ ባለሙያዎች በመጋቢት ወር ካይሮ ላይ ሲገናኙ ከመወያያ አጀንዳዎቹ መካከል አንዱ ይህ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ግድቡ ስለሚያስከትለው ጉዳትም ሆነ ስለሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ጥናት የሚካሄደው የፈረሳይ አጥኝ ቡድን ስራውን እያካሄደ መሆኑ ታውቋል።

ዝርዝር ዜና ከፍኖተ  ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ያንብቡ…