ከዐድዋ እና ከማይጨዉ ጦርነቶችና ድሎች ምን እንማራለን? መማር ከቻልን

ከበቀለ ገሠሠ (ዶ/ር) –  የአድዋ ጦርነት ድላችን ከፍተኛ ክብርና ኩራት ያጎናፀፈን ከመሆኑም በላይ ለዓለም ጭቁኖች በሙሉ የነፃነት ትግሎች ከፍተኛ ምሣሌ ጥሎ ያለፈ ተዓምራዊ ክንዋኔ ነበር። የማይጨዉም እልህ አስጨራሽ ትግልና ነፃነት እንደዚሁ። ጣሊያ እኮ በሁለቱም ጦርነቶች ወደአገራችን የዘመተችዉ የራሷን ጥቅም ለማስፋፋት ነበር። ይሄን ደግሞ የተማረችዉ ከርሷ በፊት የአፍሪቃን፤ የኢስያን፣  የፓሲፊክንና የአሜሪካን አገሮች ከተቀራመቱት እንግሊዞች፤ ጀርመኖች፤ እስፓኛዎችና ፖርቹጋሎች በመማር ነበር። የቤርሊን ጉባኤ በመባል በሚታወቀዉ ሴይጣናዊ ስምምነት ላይ የተደረሰ ዉሳኔ በመሆኑ ጣሊያም እንዳበደች ዉሻ እያለከለከች ወደ እኛ አገር ያቀናችዉ ድርሻዋን ልትቀራምት ነበር። በዓለም ላይ ይሄን ቅርምት ያልፈቀደች፤ ያልተበገረችና ነፃነቷን ጠብቃ እስካሁን የቆየችዋ አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት።  ሙሉውን ያንብቡ