የወንዙን ዉሃ ምን ያስጮኸዋል?

በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ:  ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፤ያገር ያለህ ! የዳኛ ያለህ ! የህግ ያለህ! የመንግሥት ያለህ ! እያለ ይጮኻል።  ሀገርም፤ ዳኛም፤ መንግሥትም እንደሌለው ልቡ እያወቀው፤ ጩኸቱን የሚሰማለት አገኛለሁ ብሎ ግን ዕሪታውን ቀጥሏል። ሀገርና ሕዝብ አኩርፈዋል።  ተቀይመዋል።  ተቀያይመዋል። ተሸሽገዋል።  ተደብቀዋል።  መላ-ቅጡ ጠፍቷቸዋል። ቅስማቸው ተሰብሮ፤ አንገታቸውን ደፍተዋል።  ሰማይ -ምድሩም ተደፍቶባቸዋል። እርስ- በእርሳቸው እንዳይወያዩ፤ እንዳይመካከሩ፤ ፊት ተዘዋውረዋል። ተኮራርፈዋል።  የጋራ መንግሥትና ህግ፤ ዳኛና ፍትኅ-ርትዕ በመጣታቸው፤ በአውላላ ሜዳ ላይ ይማልላሉ።  ይዋልላሉ።  አቃፊ-ሰብሳቢ መንግሥት አጥተው፤ በበታኝ ሥርዓት፤ ተበታትነዋል።  ከሀገራቸው ዕትብት ጋር እንዲቆራረጡ እየተደረጉ ነው።  ሀገራቸውም፤ ስሟ ብቻ እንጅ፤ ጨገሬታዋ እንደለለ ተቆጥሯል። ኢትዮጵያና ሕዝቧ ጮኸታቸውን የሚያዳምጥላቸው ታዛቢ አላገኙም።  ሙሉውን ያንብቡ