ሕዝባዊ ዐመጽና የሥርዓት ለውጥ

ዴሞክራሲያ (ቅጽ 42 ቁ. 4 ጥር/ የካቲት 2009 ዓ.ም): የአገራችን የቅርብ ታሪክ በየካቲት ወር ውስጥ አስደሳችም አሳዛኝም ሁኔታዎች እንደተፈጸሙ ይነግረናል። በየካቲት ወር የኢትዮጵያ ነጻነትና ሉዓላዊነትን ያረጋገጡ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያኮሩ፤ ለመብቱ ለእድገቱና ለብልጽግናው የተስፋ ጭላንጭል ያሳዩ ክስተቶች የተፈጽሙ እንደመሆናቸው ሁሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተጨፈጨፉበትና መስዋዕት የሆኑበት፤ ከፋፋዩና አምባገነኑ ዘረኛ ቡድን ውልደት ያገኘበት አሳዛኝ ወር እንደነበርም ተገንዝበናል። በየካቲት 23 1888 ዓ.ም የተከናውነውን የዓድዋ የድል በዓል እና በየካቲት 66 የአጼውን አፋኝ አገዛዝ የገረሰሰውን የ1966-ኡን የለውጥ እንቅስቃሴ በደስታና በሆታ ስናከብር በየካቲት 12 በአዲስ አበባ በግራዚያኒ ፋሽስቶች በግፍ የተጨፈጨፉትን ወይንም ዘረኛውና ጨፍጫፊው የወያኔ ቡድን ነፍስ የዘራበትንና ህልውና ያገኘበትን ክስተት በሀዘን እናስባለን።  ሙሉውን ያንብቡ